ባለስልጣኑ ወንዞችና የወንዞች ዳርቻ የበከለው ዲ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ባለስልጣኑ ወንዞችና የወንዞች ዳርቻ የበከለው ዲሊኦፖል ኢንተራሽናል ሆቴል 600,000(ስድስት መቶ ሺህ) ብር መቅጣቱ አስታወቀ

የአዲስ አበባ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በካይ የፍሳሽ ቆሻሻን ወደ ወንዝና የወንዝ ዳርቻ የለቀቀው ዲሊኦፖል ኢንተራሽናል ሆቴል ከአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ጋር በመተባበር 600,000/ስድስት መቶ ሺህ/ ብር የቅጣት እርምጃ መውሰዱን አስታውቋል።

ድርጊቱ በቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 1 ልዩ ቦታው ባንቢስ አከባቢ ወደ ወንዝ የሽንትቤት ፍሳሽ በመልቀቅ ብክለቱን ከአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ምርመራ በመረጋገጡ ከዚህ ቀደም እርምጃ የተወሰደ ሲሆን አሁንም በድጋሚ በመልቀቁ የቅጣቱን እጥፍ ተቀቷል።

ከቅጣቱ በተጨማሪ ብክለቱ ለማስቆም ችግሩ እስኪስተካከል የሆቴሉ የችግሩ መንስኤ የሆኑ መጸዳጃ ቤቶቹ እንዲታሸግ መደረጉ ተገልጿል።

ባለስልጣኑ በከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ ወጪ በማውጣት ወንዝና የወንዝ ዳርቻዎች እየለሙ መሆኑ በመግለፅ ወንዞቹን በመበከል ለታለመለት አላማ እንዳይውል በሚያደርጉ ግለሰቦች እና ድርጅቶች የሚወስደው አስተዳደራዊ እርምጃ አጠናክሮ የሚቀጥል አሳውቋል።

ባለስልጣኑ ከተማው ነዋሪዎችና ተቋማት በደንቡ ዙሪያ ሰፊ ግንዛቤ መፍጠሩ አስታውሶ ነዋሪዎችና ተቋማት ከመሰል ተግባራቸው እንዲታቆጠቡ አሳስቧል።

ህብረተሰቡ ለማንኛውም አይነት የደንብ መተላለፍ በነፃ ስልክ 9995 መረጃና ጥቆማ እንዲሰጥ ጥሪውን ያቀርባል።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.