pSrntdoeso8f8a34glhmmmh61510t4...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

pSrntdoeso8f8a34glhmmmh61510t43l5h0t461 1 903a h 46372698t03luu2 · የቀዳማይ ልጅነት ልማት አበባ እና አዝመራው፣ ከዛሬ ተሻግሮ በትውልዶች የሚሰበሰብ የሀገር ግንባታ ነው።

ዛሬ ዓለም አቀፍ የቀዳማይ ልጅነት ጉባኤን አስጀምረናል።

ኢትዮጵያ ለልማት በምታደርገው ቆራጥ ጥረት ውስጥ የሰው ተኮር የልማት አቅጣጫ ቅድሚያ ከሚሰጣቸው ዋና ጉዳዮች አንዱ ነው።

መንግሥት መጪው ትውልድ ጤናማ፣ ብቁ እና ውጤታማ እንዲሆን የቀዳማይ ልጅነት ፕሮግራምን ማዕከል በማድረግ ሁሉን አቀፍ ሥራን እየተገበረ ነው። የልጆች ትምህርት ቤቶችን ማስፋፋት፣ የምገባ ሥርዓት፣ የሕጻናት መጫወቻ ሥፍራዎች ግንባታ ላይ ተጨባጭ ውጤቶች አምጥቷል።

ሀገር አቀፍ የቀዳማይ ልጅነት ልማት እና ትምህርት ፖሊሲ የዘላቂ ብልጽግና መንገዳችን ከሆነው የመደመር እሳቤ ጋር በተናበበ መልኩ እየተተገበረ በስኬት ቀጥሏል።

በመላ ሀገሪቱ ከ35 ሺህ በላይ የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን በማስፋፋት የነጻና አስገዳጅ ትምህርት ተደራሽ እንዲሆን እያደረግን ነው።

ልጆች ላይ መሥራት በነገ ሀገር ላይ መሥራት በመሆኑ ይሄንን ትውልድ አስቀጥል ወሳኝ ተግባር ተባብረን፣ በጊዜ የለንም መንፈስና በትጋት እንድንሠራ በድጋሜ አደራ ለማለት እፈልጋለሁ፡፡


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.