ባለስልጣኑ በኮሪደር መሠረተ ልማት ላይ ጉዳት ያ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ባለስልጣኑ በኮሪደር መሠረተ ልማት ላይ ጉዳት ያደረሱ የግንባታ ድርጅትና ሹፌሮች 410,000 ሺህ ብር መቅጣቱን አስታወቀ!

ባለስልጣኑ በኮሪደር መሠረተ ልማት ላይ ጉዳት ያደረሱ የግንባታ ድርጅትና ሹፌሮች 410,000 ሺህ ብር መቅጣቱን አስታወቀ!

የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 ማህሙድ ሙዚቃ ቤት አካባቢ በልማት ኮሪደር በተሰራው የመንገድ መሠረተ ልማት ላይ ጉዳት ያደረሱ የግንባታ ድርጅትና ሹፌሮች በድምሩ 410,000 ሺህ ብር መቀጣቱ አስታወቀ መቅጣቱን አስታወቀ ።

ቅጣቱ ጉዳት ያደረሱት ምንሀር ኮንስትራክሽን የግንባታ ድርጅት 300,000/ሦስት መቶ ሺህ/ ብር ሲቀጣ አሽከርካሪዎቹ እንደ ጥፋታቸው በድምሩ 110,000/አንድ መቶ አስር ሺህ ብር ተቀጥተው በድምሩ 410,000 ሺህ ብር በመቅጣት ለከተማው ልማት ስራ እንዲውል የተደረገ ሲሆን ያቆሸሹትን አስፖልት ወዲያውኑ እንዲያፀዱ ተደርጓል።

ባለስልጣኑ በከተማው ደንብ የሚተላለፉ እና መሠረተ ልማት የሚያበላሹ ድርጅቶች እና ግለሰቦች ላይ በህጉ መሠረት የሚወስደውን እርምጃ አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አስታውቋል ።

ማህበረሰቡ ለማንኛውም የደንብ መተላለፎች መረጃ በ9995 ነፃ የስልክ መስመር ጥቆማ እንዲሰጥ ተቋሙ ጥሪውን ያቀርባል።

መረጃው :- የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣ


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.