ዛሬ የኦሲስ አጠቃላይ ሆስፒታልን መርቀን ሥራ አስጀምረናል።
የኦሲስ አጠቃላይ ሆስፒታል ለሀገራችን ጥራት ያለው ሕክምና ለማቅረብ አማራጭ ይዞ የመጣ ማዕከል ነው።
አቅም ያላቸው ውጭ ሀገር ድረስ በመሄድ መታከም ይችላሉ፤ አቅም የሌላቸው ዜጎቻችን ደግም በሃገር ውስጥ ታክመው እንዲድኑ በመንግስትና በግሉ ዘርፍ ትብብር ዘመኑን የዋጁ ሆስፒታሎች እንዲገነቡ እያደረግን ነው።
ተቋሙ አዲስ አበባን የጤና ቱሪዝም ማዕከል ለማድረግ ለጀመርነው ጉዞ ተጨማሪ አቅም የሚፈጥር በመሆኑ ስኬታማ እንዲሆን እመኛለሁ።
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ሕዝቦቿን ይባርክ!
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.