የኑሮ ውድነት መናር እና የገበያ ቁጥጥርን በተመ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

የኑሮ ውድነት መናር እና የገበያ ቁጥጥርን በተመለከተ፥ ከተማ አስተዳደሩ በርካታ ተግባራትን አከናውኗል! አቶ ጃንጥራር አባይ ምክትል ከንቲባ እና የኢዱስትሪ ልማት ቢሮ ሃላፊ

የኑሮ ውድነት መናር እና የገበያ ቁጥጥርን በተመለከተ፥ ከተማ አስተዳደሩ በርካታ ተግባራትን አከናውኗል! 

አቶ ጃንጥራር አባይ 
ምክትል ከንቲባ እና የኢዱስትሪ ልማት ቢሮ ሃላፊ

👉የመሰረተ ልማት አቅርቦት ከማሻሻል እና ከማስፋት አኳያ 6 የገበያ ማእከላት በሙሉ ለምርት አቅርቦት ምቹ እንዲሆኑ ተደርጓል

👉250 በላይ የሰንበት ገበያዎችን ማስፋት ምርቶችን ከአምራቾች በቀጥታ ለህብረተሰቡ እንዲቀርቡ ተደርጓል። ይህም የትራንስፖርት ወጪን ከመቀነሱም በላይ፣ በበዓላት ወቅት ሊያጋጥም የሚችልን የምርት እጥረት ለመፍታት አስችሏል።

👉በከተማ ግብርና፣ በህብረት ሥራ ማህበራት እና በንግድ ስራዎች ድርጅት በኩል የአቅርቦት ሰንሰለቱን ለማጠናከር ሰፊ ስራ ተሰርቷል። በተለይም የዘይትና መሰል መሠረታዊ ፍጆታዎች አቅርቦት ላይ ትኩረት ተሰጥቷል።

👉በከተማ ግብርና  እንቅስቃሴ በተሰራው ስራ በዓል ግብይት ላይ በተለይ የመንግስት ሰራተኛው በሸማች በኩል እንዲያገኙ ተደርጓል።

👉የንግድ ስራዎች ድርጅትን አቅም በማጠናከር የስኳር፣ዱቄት ምርቶችንና ዘይት አቅርቦት በተለይም በ 2400ይሸጥ የነበረውን ዘይት በ1680 እንዲቀርብ የሚያስችል ግዢ በመፈጸም በንግድ ስራዎች ድርጅት እንዲቀርብ ማድረግ ተችሏል።

 👉በገበያው ላይ የሚታዩ ህገ-ወጥ ድርጊቶችን ለመከላከል በተደረገ ቁጥጥር፣ በአስተዳደራዊ እና በህጋዊ መንገድ ከ 18 ሺህ በላይ እርምጃዎች ተወስደዋል። ይህም የቁጥጥር ስራው አበረታች ውጤት እያመጣ መሆኑን ያሳያል።

👉የማህበራትና የንግድ ተቋማትን አቅም የማሳደግ ተኪ ምርቶችን ማሳደግ ትኩረት አሁንም የሚሰጠዉ ነዉ፡፡ አቅማቸዉን ለመፍታት ከተማ አስተዳደሩ ቁርጠኛ አቋም ወስዶ እየተሰራ ነዉ። ከህዝብ ትራንስፖርት አኳያ 43 በመቶ በላይ እያደገ ስለሆነ አዉቶብሶችን መግዛት ብቻ ሳሆን ቅሚያ ለህዝብ በሚል ነዳጅ እንዲያገኙ እየተደረገ ነዉ፡፡

👉የነዳጅ አቅርቦት በተመለከተ ወደ ቴክኖሎጂ በማስገባት አዳዲስ ፈጠራዎችን በማድርግ በጋራ እየተሰራ ነዉ ፡፡

👉ኑሮ ውድነት ከማረጋጋት አንፃር በከተማችን አዲስ አበባ በርካታ ስራዎች የተሰሩ ሲሆን በዋናነት በቤት ልማት ፣በስራ እድል ፈጠራ፣በምገባ ማዕከላት፣ በተማሪዎች ምገባ ፣ በበጎ ፈቃድ አገልግሎት፣ በጤና መድን አገልግሎት፣ በከተማ አውቶብስ አቅርቦት፣በፐብሊክ ትራንስፖርት አቅርቦት ሁሉ የሚደረጉ የድጎማ ስርዓቶች ሁሉ የኑሮ ውድነት ችግርን ለመቀነስ የራሳቸው አበርክቶ አላቸው፡፡


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.