በመዲናዋ በጤናው ዘርፍ የመቶ ዓመታት ጉዞን በጥ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

በመዲናዋ በጤናው ዘርፍ የመቶ ዓመታት ጉዞን በጥቂት ዓመታት ማከናወን ተችሏል- ከንቲባ አዳነች አቤቤ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባለፉት ጥቂት ዓመታት በጤናው ዘርፍ ያስመዘገበው የልማት ሥራ፣ ባለፉት መቶ ዓመታት ከተከናወኑት ተግባራት ጋር እኩል መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ። 

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የ5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 3ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ ፣ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከምክር ቤት አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

ከተማዋን ለነዋሪዎቿ ምቹ፣ ጽዱ እና ጤናማ ለማድረግ የሚከናወኑት ሥራዎች አዲስ አበባን በዓለም አቀፍ ደረጃ ተሸላሚ እያደረጓት እንደሚገኙም አንስተዋል።

የከተማ አስተዳደሩ ትኩረት ካደረገባቸው ዋና ዋና ጉዳዮች መካከል የጤና መሰረተ ልማትን ማስፋፋት አንዱ ሲሆን፣ በዚህም ተጨባጭ ውጤቶች ተመዝግበዋል ብለዋል።

በዚህም ባለፉት ጥቂት ዓመታት ብቻ የተገነቡት የጤና ተቋማት የከተማዋን የጤና መሰረተ ልማት በሁለት እጥፍ እንዳሳደጉት ገልጸዋል።

አበበች ጎበና ሆስፒታል፦ ለእናቶችና ህፃናት ብቻ ተለይቶ የተገነባ ዘመናዊ አገልግሎት መስጠት የጀመረ ትልቅ ተቋም ነው።

በሀገሪቱ የመጀመሪያ የሆነው የተቀናጀ የአንጎልና ህብለሰረሰር ቀዶ ጥገና ማዕከል የተገነባበት የዘውዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታል፣ በተጨማሪም የሆስፒታሉን አቅም በእጥፍ የሚያሳድግ የ320 አልጋዎች ህንፃ ተገንብቶ መጠናቀቁን ነው የገለጹት።

ባለ 10 ወለል አዲስ ህንፃ ተገንብቶለት አገልግሎት የጀመረው ራስ ደስታ ዳምጠው ሆስፒታል፣ የራሱ የኦክስጅን ማምረቻ ፋብሪካም እየተገጠመለት እንደሚገኝም አመልክተዋል።

በዳግማዊ ሚኒሊክ ሆስፒታል የዓይን እና የኩላሊት እጥበት ማዕከል እንዲሁም በኮልፌና በገላን እየተገነቡ ያሉ ዘመናዊ የድንገተኛ አደጋ ህክምና ማዕከላት የከተማዋን የህክምና ጥራት ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሸጋግሩ አዳዲስ ማዕከላት መሆናቸውንም አብራርተዋል።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.