የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የስራ ዘመን 3ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ ከምክር ቤቱ አባላት ከተነሱ ጥያቄዎች መካከል
👉 በመዲናዋ የጤና አገልግሎትን ተደራሽ ከማድረግና ከማዘመን ረገድ በርካታ ስራዎች ተከናዉነዋል፡፡ ነገር ግን አገልግሎቱ ባልተዳረሰባቸዉ አንዳንድ አካባቢዎች የጤና ጣቢያዎችን ተደራሽ ከማድረግ ፣ አገልግሎቱን ከማሻሻል እና ግብዓቶችን ከማሟላት ረገድ ምን ታስቧል ?
👉 በአዲስ አበባ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት አሰጣጥን ምቹ፤ ተደራሽና ዘመናዊ ከማድረግ ረገድ በርካታ ስራዎች ተከናዉነዋል፡፡ ይሁን እንጂ በአንዳንድ ወረዳዎች ከህዝብ ብዛት የተነሳ ህብረተሰቡ በቂ የአውቶቡስ አገልግሎት ማግኘት አልቻለም፡፡ በመሆኑም ህብረተሰቡ በቂ የትራንስፓርት አገልግሎት እንዲያገኝ ምን ታቅዷል?
👉 የመንግስት አገልግሎትን ለማዘመን በርካታ ስራዎች ተከናዉነዋል፡፡ ነገር ግን አሁንም ከአገልግሎት አሰጣጥ ጋር ተያይዞ ያልተፈቱ ችግሮች አሉ፡፡ የከተማ አስተዳደሩ ለህብረተሰቡ በአግባቡ አገልግሎት በማይሰጡ አካላት ላይ ምን አይነት እርምጃ እየወሰደ ነዉ?
👉:በከተማዋ የምርት አቅርቦትን ለማሳለጥና ዋጋን ለማረጋጋት በርካታ ስራዎች ተከናዉነዋል፡፡ ይሁን እንጂ አሁንም ያለ አግባብ በምርቶች ላይ ዋጋ የሚጨምሩ አካላት አሉ፡፡ በዘርፉ የሚታየዉን ችግር ለመቅረፍ ምን ታስቧል ?
👉 የከተማ አስተዳደሩ የኑሮ ውድነቱን ለማቃለል በርካታ ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል፡፡ ነገር ግን አሁን ከሚታየዉ የኑሮ ዉድነት አንጻር ተጨማሪ መፍትሔዎችን ለመስጠት ምን ታቅዷል?
👉 በኮሪደር ልማቱ ምቹ የእግረኛና የተሽከርካሪ መንገዶች ተገንብተዋል፡፡ ይሁን እንጂ አንዳንድ አሽከርካሪዎች ምቹ ሆነዉ በተገነቡ መንገዶች ላይ በፍጥነት በማሽከርከር በህብረተሰቡ ላይ አደጋ በማድረስ ላይ ይገኛሉ፡፡ ይህንን አደጋ ለመቀነስ የከተማ አስተዳደሩ ምን የመፍትሔ እርምጃዎችን እየወሰደ ነው?
👉 በኮሪደር ልማቱ ስፋት ያላቸው የመብራት መሰረተ ልማቶች ቢዘረጉም አሁንም ተደራሽ ያልሆኑ አካባቢዎች አሉና እነሱን ተደራሽ ለማድረግ ምን ለመስራት ታቅዷል?
👉 ትውልዱን በስነ አእምሮና በጥበብ ለመቅረጽ የሚያስችሉ የተለያዩ ተቋማት እየተገነቡ ይገኛሉ፡፡ የተጀመረዉን ስራ ለማስቀጠል ምን ታስቧል?
👉 በመዲናዋ ከአሁን በፊት የሚታየዉን የጎርፍ ስጋት ለመቀነስ በተወሰደዉ እርምጃ በርካታ ለዉጦች ታይተዋል፡፡ አሁንም ለጎርፍ ተጋላጭ የሆኑ አካባቢዎች አሉ፡፡ እነዚህን አካባቢዎች የኮሪደር ልማት ሥራ አካል ለማድረግ ምን ታቅዷል?
👉 በስፖርት ልማት ዘርፍ አመርቂ የልማት ስራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ፡፡ የተጀመሩትን ስራዎች አጠናክሮ ከማስቀጠል፤ የወጣቶችን የአካልና የአእምሮ ጤንነት ከመጠበቅ፤ ወጣቶች አምራች ሆነው በስፖርቱ ዘርፍም በዓለም አቀፍ ደረጃ የሀገራቸውን ስም እንዲያስጠሩ ምን ታስቧል?
👉 በነዳጅ አቅርቦትና ስርጭት ላይ ቁጥጥርና ክትትል እየተደረገ፤ ለህዝብ የትራንስፖርት አገልግሎት ለሚሰጡት ቅድሚያ እንዲሰጥ የተወሰነ ቢሆንም የነዳጅ ስርጭት እንዲስተጓጎል የሚያደርጉና በድብቅ ነዳጅ የሚሸጡ አካላት አሉ፡፡ እነዚህን ተከታትሎ እርምጃ ከመዉሰድ ረገድ ምን እየተሰራ ይገኛል?
👉 ነዳጅ አቅርቦት ላይ ከተማ አስተዳደሩ እያከናወነ ያለው ሥራ ካለ እንዲሁም ለቀጣይ ምን ታስቧል?
👉 የቤት አቅርቦት ችግርን በዘላቂነት ለመፍታት ምን ታስቧል?
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.