‎''የሚዲያ እመርታ ለትርክት ግንባታ'' በሚል...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

‎''የሚዲያ እመርታ ለትርክት ግንባታ'' በሚል መሪ ቃል በተዘጋጀውና ባለፉት ዓመታት በሚዲያ ዘርፍና ተቋማት ላይ የተመዘገቡ ስኬቶች በቀረቡበት የምክክር መድረክ ላይ ታድሜ ሀሳቤን አጋርቻለሁ። ‎

''የሚዲያ እመርታ ለትርክት ግንባታ'' በሚል መሪ ቃል በተዘጋጀውና ባለፉት ዓመታት በሚዲያ ዘርፍና ተቋማት ላይ የተመዘገቡ ስኬቶች በቀረቡበት የምክክር መድረክ ላይ ታድሜ ሀሳቤን አጋርቻለሁ።

‎ባለፉት ስምንት ዓመታት የሚዲያ ምህዳሩን በዲሞክራሲያዊ አውድ ለመዋጀት በወሰድነው እርምጃ ለሀገር ግንባታ የሚረዳ መሠረት ጥሏል። ይህ ውጤት እንዲቀጥልም ሚዲያዎች ከዋልታ ረገጥነትና ከጽንፈኝነት ወጥተው በእውነት ላይ የተመሠረተ ትርክት በመገንባት፣ ለጋራ ማንነትና ለብሔራዊ መግባባት በቁርጠኝነት ሊሠሩ ይገባል።

‎ሚዲያዎቻችን በሰው ሰራሽ አስተውሎት እና በጥናት የታገዘ ጥልቅ ትንተና በማቅረብ፣ ከአርዕስት ሽያጭ ባለፈ ለሀገር አጀንዳዎች ትኩረት መስጠት ይኖርባቸዋል። ተግባራቸውም በዓላማ፣ በእይታ፣ በሙያዊ ብቃትና ለህዝብ ቅርብ በመሆን ላይ ተመስርቶ፣ ሚዛናዊነትን በጠበቀ መልኩ ለሀገር ብልጽግና መንገድ ጠራጊና ችግር ፈቺ ሆነው ሊቀጥሉ ይገባል።"

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

የናሽናል ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ብሩክ ከበደ ''የሚዲያ እመርታ ለትርክት ግንባታ'' በተሰኘው ሀገራዊ የምክክር መድረክ ላይ በዘርፉ በተለይም በኤንቢሲ ጣቢያ የተመዘገቡትን የለውጡን ስኬቶች አንስተዋል። ለውጡ ትኩረቱን በዋነኛነት በእሳቤ፣ በህግና አሰራር ላይ በማድረግ፣ ተቋማዊ ብቃትና ሥነ ምግባርን ማጎልበት፣ ለዲጂታላይዜሽን ቅድሚያ በመስጠት፣ የመረጃ ንፉግነትን ባህል በመቀየርና የወል ትርክት በመገንባት ተቀዳሚ የሚዲያ ተቋም መሆን ችሏል።

የአዋሽ ኤፍ ኤም ዋና ስራ አስኪያጅ ዶ/ር አብዱ መሀመድ ''የሚዲያ እመርታ ለትርክት ግንባታ'' በተሰኘው ሀገራዊ የምክክር መድረክ ላይ የለውጡ መንግሥት ለዘርፉ ያበረከታቸውን ትሩፋቶች አብራርተዋል። የቁጥጥር እና የፖለቲካ ገደቦች፣ የአቅምና የሙያ ክፍተቶች፣ የፋይናንስና የቴክኖሎጂ ገደቦች ዘርፉንና ተቋሙን ሲፈትኑ የከረሙ ስር የሰደዱ ችግሮች እንደነበሩ አንስተዋል። እነዚህ ችግሮች የፖሊሲ እና የህግ ማሻሻያዎችን በማድረግ፣ ለኢንቨስትመንት ትኩረት በመስጠት የሬዲዮ ጣቢያዎች ከመበራከታቸው ባለፈ የጋራ እሴቶችን በማጠናከር እና ማህበረሰብን በማስተሳሰር እንዲሁም ሀገርን በመገንባት ሂደት ውስጥ ወሳኝ ሚናቸውን እንዲጫወቱ አስችሏል።

የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አድማሱ ዳምጠው ''የሚዲያ እመርታ ለትርክት ግንባታ'' በተሰኘው የዘርፉ የምክክር መድረክ ላይ በሚዲያው ዘርፍ የለውጡ መንግስት ያስመዘገባቸው ስኬቶችን ለተቋሙ ያለውን አበርክቶ በጥልቀት አቅርበዋል።

ተቋሙ ሰፊውን ሪፎርም በመቀላቀል ብቁ፣ ተወዳዳሪና ሙያዊ ነጻነቱ የተከበረ ማድረግ ችሏል።

‎በይዘት፣ በተለወጠ አደረጃጀት እና በቴክኖሎጂ አማራጮች ተደራሽ በመሆን ተወዳዳሪነቱን አስፍቷል። ተቋሙ ከሪፎርሙ በመቋደሱ ከራሱ አልፎ ሰፊ የብሮድካስት ልምዱን በማካፈል ላይ ይገኛል። በተጨማሪም ፈጠራን፣ የሀሳብ ብዝሀነትና አለም አቀፋዊነትን በማስፋት ተመራጭና ወቅታዊ የመረጃ ምንጭ በመሆን እያገለገለ ይገኛል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ዋና ስራ አስኪያጅ ሰይፈ ደርቤ ''የሚዲያ እመርታ ለትርክት ግንባታ'' በተሰኘው ሀገራዊ የምክክር መድረክ ላይ እንዳቀረቡት የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ከምስረታው ባልተናነሰ የለውጡ መንግሥት በዘረፉና በተቋሙ ባደረገው ሪፎርም ምክንያት ዳግም ተወልዷል ማለት እንደሚቻል ገልጸዋል።

‎የተከናወነው የእሳቤ፣ የህግና አደረጃጀት እንዲሁም የአሰራር ሪፎርም፤ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎትን በአፍሪካ አስተማማኝና ተጽዕኖ ፈጣሪ የዜና ምንጭ በመሆን ብሄራዊ ጥቅምን ማስጠበቅና ብሄራዊ መግባባት መፍጠር የሚያስችል አቅም እንዲላበስ አስችሎታል። ተቋሙ ተደራሽነቱን በማስፋት፣ በቴክኖሎጂ ተደራጅቶ፣ ከኢትዮጵያ ተሻግሮ የአፍሪካ ድምጽ በመሆን የወል ትርክትን እየገነባ ይገኛል።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.