የሚሰሩ እጆችን እናበረታታለን!
የድህነታችን ቋጠሮ የሚፈታው ሁላችንም በርትተን ስንሰራ ነው።
ዛሬ ለ1,278 ኢንተርፕራይዞች የመስሪያ ቦታ ሼዶች አስተላልፈናል።
በዚህም 3,889 እንቀሳቃሾች ተጠቃሚ ሆነዋል።
አብዛኞቹ ሼዶች በፍጥነትና በጥራት በአጭር ጊዜ ተገንብተው ለተጠቃሚዎች የተላለፉ ናቸው።
በከተማችን የስራ ባህል እንዲቀየር፣ ለስራ የሚተጋ ትውልድ ለመፍጠር፣ በግል ጥረት ራስን መቻልን እና ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የማያቋረጥ ሥራ እየሰራን ነው።
ችግሮችን ብቻ በማውራት ከድህነት መላቀቅ አይቻልም። ከድህነት መላቀቅ የሚቻለው በተገኘው እድል እልህ ውስጥ ገብተን ስንሰራ ብቻ ነው ። ድህነት የሚፈታው በመንግስት ብቻ አይደለም፤ ይልቁንም የሁላችንንም ጥረት ይጠይቃል።
ዛሬ የመስሪያ ቦታ ያገኛችሁ፣ በልቶ ከማደር ባሻገር ከመንግሥት ያገኛችሁትን ድጋፍ ተጠቅማችሁ እልህ ውስጥ በመግባት ተግታችሁ በመስራት የትላልቅ ኩባንያ ባለቤት እንድትሆኑ ይጠበቃል።
ተደራጅታችኋል፤ ሰልጥናችኋል፤ በጋራ ለማደግ፣ በጋራ ለመለወጥ፣ ለሀገር እድገት የበኩላችሁን አስተዋፅዖ ማበርከት እንድትችሉም አደራ እላለሁ።
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ!
አዳነች አቤቤ
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.