ሀገር በልጆቿ ጥረትና ትጋት ትገነባለች!
ዛሬ በከተማችን በውቧ አራዳ ፓርክ ለተከታታይ 3 ቀናት የሚቆይ ከተማ አቀፍ የቴክኒክና ሙያ ሳምንት ዓውደ-ርዕይ ክፍት እድርገናል።
“የቴክኖሎጂ ልህቀት ለሀገር ብልጽግና!” በሚል መሪ ቃል ለ16ኛ ጊዜ በምናካሂደው በዚህ የቴክኒክና ሙያ ሳምንት፣ የብልፅግና ተምሳሌት የሆነችው ከተማችን አዲስ አበባ በዘርፉ ያላትን ተወዳዳሪነት በተግባር የምናሳይበት ነው።
የሚሰሩ እጆች፤ የሚፈጥሩ አዕምሮዎች ለሀገር ግንባታ ትልቅ መሰረትን ይጥላሉ። ሀገራችን በዚህ ወቅት በቴክኖሎጂ ፈጠራ፣ በቴክኖሎጂ መቅዳት እና መልሶ በመጠቀም የዓለምን ፈጣን እድገት መቀላቀል ችላለች።
ትላንትና ተኪ ምርቶችን ባለማምረታችንና በውጭ ምንዛሪ እጥረት የምንፈልገውን ፈጣን እድገት ማስመዝገብ ላይ የነበረውን ውስንነት በመቅረፍ ትላልቅ ለውጦችን እያስመዘገብን እንገኛለን።
በከተማችን ፈጣን እድገት ግንባታ ሂደት ውስጥ ቴክኒክና ሙያ ተቋማት ትልቅ አስተዋጽኦ አላቸው። ሀገራችን እንደዚህ ዓይነት ፈጣሪ እጆች የምትፈልግበት ወቅት ላይ እንገኛለን። ከቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ከዚህ በላይ ትጠብቃለችና በ24/7 የተለወጠ የስራ ባህል በመስራት ውጤቶችን ማስመዝገብና ማስፋትን አጠናክራችሁ ቀጥሉ።
ከተማ አስተዳደራችንም ሁሌም ጥረታችሁ ለውጤት እንዲበቃ ያልተቋረጠ ድጋፍ ያደርጋል።
ዓውደ-ርዕዩን በዚህ ልክ በተደራጀና በተቀናጀ መልኩ ያዘጋጃችሁ የሥራ እና ክህሎት ቢሮ አመራሮች፥ የቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች መምህራንና ሠራተኞች እንዲሁም ተማሪዎች እናመሰግናቹሃለን።
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.