በአዲስ አበባ በተካሄደው ዛይድ የደግነት ሩጫ የ5 ኪ.ሜ ውድድር በወንዶች ንብረት ክንዴ እና በሴቶች አለሽኝ ባወቀ አሸናፊ ሆኑ
በአዲስ አበባ በተካሄደው ዛይድ የደግነት ሩጫ የ5 ኪ.ሜ ውድድር በወንዶች ንብረት ክንዴ እና በሴቶች አለሽኝ ባወቀ አሸናፊ ሆነዋል፡፡
የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ መስራች የሆኑትን የሼህ ዛይድ ቢን ሱልጣን አል ናህያንን ሰብአዊ ራዕይ መነሻ በማድረግ የተዘጋጀ ታዋቂው ዛይድ የደግነት ሩጫ ውድድር በአዲስ አበባ ከተማ ተካሂዷል፡፡
በውድድሩ ከወንዶች ንብረት ክንዴ አንደኛ በመውጣት ውድድሩን ያጠናቀቀ ሲሆን ኡርጌሳ ነጋሳ ሁለተኛ ደረጃ እንዲሁም ግዛቸው ሙሴ ሶስተኛ በመውጣት ውድድሩን አሸንፈዋል፡፡
ከሴቶች ደግሞ አለሽኝ ባወቀ አንደኛ ደረጃ፣ ሽቶ ጉሚ ሁለተኛ፣ ሮቤ ዲዳ ሶስተኛ ደረጃ በመያዝ አሸናፊ ሆነዋል፡፡
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.