ዛሬ በመዲናችን ከ500 በላይ የሳይክል ተወዳዳሪ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ዛሬ በመዲናችን ከ500 በላይ የሳይክል ተወዳዳሪዎች የተሳተፉበት ታላቅ የሀገር ዉስጥ ውድድር በድምቀት ተካሂዷል።

ነገም ቀጥሎ ዓለም አቀፍ ሲቲ ማውንቴን ባይክ (City Mountain Bike)በአድዋ ድል መታሰቢያ ፕላዛ ላይ የሚካሄድ በመሆኑ ደስ ብሎናል ነው።​
​በቀጣዮቹ ቀናት የምናካሂዳቸው ታላላቅ የስፓርት ሁነቶች፦

- ​ነገ ጠዋት ሚያዝያ 25/2018 ከጠዋቱ 12:00 ጀምሮ በመስቀል አደባባይ ሸህ ዝያድ የ5 ኪሎ ሜትር የበጎነት ሩጫ ይካሄዳል።
- ​ሰኞ (ሚያዝያ 26/2018) የምስራቅ አፍሪካ ዞን አምስት የእጅ ኳስ (Handball) ሻምፒዮና በድምቀት ይጀመራል።

​እነዚህ ዓለም አቀፍና አህጉራዊ ውድድሮች የከተማችን የልማት አሻራዎች የአትሌቲክስ እና የብስክሌት ስፖርቶችን ጨምሮ ለዓለም አቀፍ ሁነቶች ምቹ በመሆናቸው የስበት ማእከል ሆነናል።

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.