ምክር ቤቱ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት የቦርድ አባላትን ሹመት አጸደቀ
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት የቦርድ አባላትን ሹመት በአብላጫ ድምጽ አጽድቋል።
የቦርድ አባላቱን ሹመት አስመልክቶ ማብራሪያ የሰጡት በምክር ቤቱ የመንግስት ተጠሪ ሚኒስትር ዴኤታ ምህረቱ ሻንቆ (ዶ/ር) ተሿሚዎቹ በትምህርት ዝግጅት እንዲሁም ባዳበሩት ክህሎት የድርጅቱን ተልእኮ ማሳካት የሚችሉ መሆናቸውን ገልጸዋል።
ብሔራዊ ጥቅምን መረዳት የሚችሉ እንዲሁም ተቋሙን ለስኬት እንደሚያበቁ የታመነባቸው መሆናቸውን ተናግረዋል።
በዚህም ፦
1፡- ብሌን ማሞ ....... የቦርድ ሰብሳቢ
2፡- ፈዲላ ቢያ ....... አባል
3፡- ተስፋዬ ዘውዴ ....... አባል
4፡- መሐመድ ካሳ ....... አባል
5፡- አፈወርቅ በደዊ ....... አባል
6፡- አስማ ረዲ ....... አባል
7፡- ዮናስ በቀለ ....... አባል
8፡- ሃፍታይ ገብረእግዚአብሔር ....... አባል
9፡- ኢሳያስ ካሳ (ዶ/ር)....... አባል ሆነው እንዲሾሙ የቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ ምክር ቤቱ መርምሮ በአንድ ድምጸ ተአቅቦ በአብላጫ ድምጽ አጽድቋል።
ተሿሚዎችም በምክር ቤቱ ቀርበው ቃለ-መሀላ ፈጽመዋል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.