የስፖርት ቱሪዝም እድገት ማሳያ አዲስ አበባ !
መዲናችን አዲስ አበባ ባከናወነቻቸው አመርቂ የልማት ስራዎች የሁሉ ቀልብ ማረፊያ ሆናለች፡፡
ወንዞቿን አክማ የጎሰቀሉ እና ደሃ ነን የሚል መልዕክት ያስተላልፉ የነበሩ መንደሮቿን አፍርሳ ደረጃቸውን የጠበቁ ቤቶች ፣ መንገዶች ፣ የህፃናት መጫወጫ ስፍራዎችና የስፖርት ማዘውተሪያ ሜዳዎች እንዲሁም ቤተመፅሀፍት ገንብታ እንካችሁ ብላለች፡፡
ከተማዋ በሰራችው ለትውልድ ተሻጋሪ ስራ የሁሉም ቀልብ ማረፊ ፣ የአፍሪካውያን መቀመጫ ፣ ምቹ ፣ ለሁሉ ተስማሚ ከተማ መሆኗን ዓለም በአንድ ድምፅ እየመሰከረ ይገኛል፡፡ ለዚህ ማሳያው አገራችን ኢትዮዽያ በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ ያስተናገደቸው እና በአዲስ አበባ በድምቀት የተካሄደው የዓለም አትሌቲክስ የአንድ ቀን ሩጫ (Addis Ababa Grand Prix) ውድድርን ተጠቃሽ ነው ፡፡
ከተማዋ ያስመዘገበችውሁለንተናዊ የልማት ስራዎች እና አካታች ዘመናዊ የመሰረተ ልማት ግንባታዎች የስፖርት ቱሪዝምን በከፍተኛ ሁኔታ በማሳደግ ረገድ ጠቀሜታቸው የጎላ ነው ፡፡
ኢትዮጵያውያን በአለም አደባባይ አይችሉም የተባለውን ስማችንን የቀይረን ውብ ንፁህና እና ተስማሚ የአየር ፀባይ ያለን ጥንታዊ የሰው ዘር መገኛ ህዝቦች መሆናችንን አለም በአይኑ አይቶ እያረጋገጠ ይገኛል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.