መዲናችንን አዲስ አበባ አረንጓዴ፤ዉብ እና ፅዱ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

መዲናችንን አዲስ አበባ አረንጓዴ፤ዉብ እና ፅዱ ማድረግ የቅንጦት ሳይሆን አይቀሬዉ የከተሜነት መገለጫ ልዩ መስፈርት በመሆኑ ልናሳካዉ ችለናል፡፡

ትናንት ከመንግስት ለዉጥ በፊት እንደ አፍሪካ ህብረት ተቋም ከአዲስ አበባ ይዉጣ የተባለበት ምክንያት ከተማዋ አረንጓዴ፤ዉብ፤ፅዱ እና የዘመነች ባለመሆኗ መሆኑ የቅርብ ጊዜ ትዝታችን ነዉ፡፡

ዛሬ ግን እኛ ኢትዮጵያዉያን አረንጓዴ፤ዉብ እና ፅዱ ባልሆነ አካባቢ መኖር እጣ ፈንታችን አይደለም፤እንድንለማመደዉ ማድረግም  እንደ ሃገር ሆነ ለከተማችን ህዝብ አይመጥንም ብለን ያ! አሳፋሪ ሃሳብ እና ሙግት ዳግም ላይነሳ በአዲስ አስተሳሰብ እና የስራ ባህል ተቀብሮ ለሌሎች ሀገራት ጭምር ኩራትና ምሳሌ ሆንን እንገኛለን፡፡ 

በከተማችን ባካሄድነዉ የልማት አብዮት በመጀመሪያዎቹ ዓመታት ከ50ዎቹ ከተሞች ዉስጥ እንዷ ያልነበረችዉ መዲናችን አዲስ አበባ ዛሬ አረንጓዴ፤ዉብ እና ፅዱ መሆን በመቻሏ በአፍሪካ ከተመረጡ አስር ከተሞች አንዷ ለመሆን በቅታለች፡፡

ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በፕሮጀክቶች አፈፃፀም እና በመሰረተ-ልማት ግንባታዎች በተመዘገቡ ዉጤቶች አዲስ አበባ ዲጂታል አገልግልግሎቶችን እዉን በማድረጓ የተናበቡ፤የተቀናጁ፤የተሳለጡ፤ ፍጥነትን እና ጥራትን ማዕከል ያደረጉ አገልግሎቶችን በመስጠት የዘመነች ከተማ ለመሆን ችላለች፡፡

በተጨማሪም የመዲናዋ የኮሪደር እና የወንዞች ዳር ልማቶቿ ወደ ስማርት ሲቲነት የምታደርገዉን የከተሜነት ጉዞ የሚያፋጥኑ፤ሌሎች ሃገራት ልምድ እና ተሞክሮ የሚቀስሙባቸዉ የኢትዮጵያዉያን ህያዉ አሻራዎች ናቸዉ፡፡

በሁለተናዊ መልኩ እየተሳለጡ ያሉ የመዲናዋ ዘርፈ-ብዙ የልማት ስራዎች መንግስት እና ህዝብ በአንድ ልብ፤በተባበረ ክንድ እና በፀና አቋም  እዉቀታቸዉን፤ጉልበታቸዉን፤ገንዘባቸዉን ያዋሉባቸዉ፤ዛሬ ፍሬ አፍርተዉ በጋራ እየተቋደሱ የሚያጣጥሟቸዉ የዚች ዉብ፤ፅዱ፤ምቹ እና ታሪካዊት ከተማ ነበራዊ እዉነታዎች ሆነዋል፡፡


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.