ዛሬ የላይቤሪያ ፕሬዚዳንት ክቡር ጆሴፍ ኑማ ቦአካይን በአድዋ ድል መታሰቢያ በክብር ተቀብለናል።
ክቡር ፕሬዚዳንቱ በአድዋ ጀግኖች መታሰቢያ የአበባ ጉንጉን አስቀምጠው፣ ለመላው ጥቁር ህዝቦች ነጻነት ፋና ወጊ የሆነውን የአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም ጎብኝተዋል።
ኢትዮጵያና ላይቤሪያ ከአፍሪካ ሀገራት በቀኝ ግዛት ስር ያልወደቁ የጥቁር ህዝቦች ኩራት እና ፀረ ቀኝ ግዛት ንቅናቄ መሰረቶች መሆናቸዉ ይታወቃል ።
ክቡር ፕሬዚዳንት በምድረ ቀደምቷ ኢትዮጵያና በአፍሪካውያን ርዕሰ መዲና አዲስ አበባ የሚኖርዎ ጉብኝት የተሳካ እንዲሆን በራሴና በከተማ አስተዳደሩ ስም እመኛለሁ።
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ!
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.