ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ኢትዮጵያ የገቡትን የላይቤ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ኢትዮጵያ የገቡትን የላይቤሪያ ሪፐብሊክ ፕሬዝደንት ክቡር ጆሴፍ ንዩማ ቦአካይ በብሔራዊ ቤተ-መንግሥት አቀባበል በማድረጌ ታላቅ ክብር ይሰማኛል።

ኢትዮጵያ እና ላይቤሪያ በቅኝ ግዛት ያልተገዙ፣ ለአኅጉሩ ነፃነትና አንድነት ድምፅ በመሆን ከጋራ የጽናት ታሪክ የሚመነጭ ጥልቅና ዘመናትን የተሻገረ ግንኙነት አላቸው። ዛሬም እንደ ሁሌው ኢትዮጵያ ከሰፊ ገበታዋ ያላትን ታላቅ ዐቅምና ዘላቂ ወዳጅነት፣ አብረዋት ለሚጓዙ ሁሉ ለማካፈል ዝግጁ ናት። በዚህ መንፈስ ይህ ጉብኝት በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት በማጠናከር፤ የጋራ ህልሞቻችንን በማይናወጥ መሠረት እና የመፈጸም ቁርጠኝነት ወሳኝ ምዕራፍ እንደሚሆን ጽኑ እምነት አለኝ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.