በጥረት የደመቀች፣ ከአለም የቱሪዝም ቁንጮ ላይ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

በጥረት የደመቀች፣ ከአለም የቱሪዝም ቁንጮ ላይ የተገኘች መዲናችን

ከቃል በላይ የሆነ፣ እምቢ ብሎ ጠንክሮ መስራት ለምን ውጤት እንደሚያደርስ ያያንበት፣ በጠላት ጩኸት መሃል በድምቀት የታየ ውበትን የተላበሰች፣ ከአለም የቱሪዝም ከተሞች መሃል በቁንጮነተ መታየት የጀመረች፣ ከምንም ተነስታ ይህ የምታዩት ከቃል በላይ የሆነ ስፍራን የተላበሰች ከተማ ነች።

ይህ ሰፈር ምኑም የማይታወቅ ሰፈር ነበር። ዛሬ ግን ለአይን ማራኪ፣ ለመንፈስ አርኪ፣ ለከተማችን ጌጥ፣ ለቱሪዝም መዳረሻ፣ ለወጣቱ መዝናኛ፣ ለህፃናት መፈንጫ፣ ለአንጋፋዎች ማረፊያ፣ ለተማሪዎች ማንበቢያ፣ ለስፖርተኞች መንቀሳቀሻ፣ ለሙሽሮች መድመቂያ፣ ..... ለማንም ይሁን ትርጉም ያለው ቦታ ሆኗል።  ይህን ያየነው በአጋጣሚ አይደለም፣ በጥረት ነው። እንሰራለን ብለው በቆራጥነት በቆሙ አመራሮች እና ለህዝብ በሚያልም መንግስት የተሰራ የታሪክ ስፍራ ነው::


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.