ነገ ትልቅ እንድትሆን የምንመኝላት ኢትዮጰያ ዛሬ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ነገ ትልቅ እንድትሆን የምንመኝላት ኢትዮጰያ ዛሬ ወስደን በምንጠቀምበት የምርጫ ካርድ የሚወሰን ነዉ!!

ዛሬ ወስደን የምንጠቀምበት የምርጫ ካርድ ነገ ለምንጠይቅበት መብት፣ ለምንሻው ተጠያቂነት እና ለምንመኘው ሉዓላዊነት ብቸኛው ሕጋዊ እና ሰላማዊ መሣሪያችን ከመሆኑ ባሻገር ነገ ትልቅ እንድትሆን ለምንመኝላት ኢትዮጰያ ወሳኙ ጉዳይ ነዉ፡፡

በመሆኑም የመራጮች ምዝገባ ዜጎች የሚገቡት "ማህበራዊ ውል" ሲሆን፣ የመራጭነት ካርድ በመያዝ በጠንካራ የሀገር ግንባታ ሂደት ውስጥ ተመልካች ከመሆን ወጥቶ ውሳኔ ሰጪ መሆን ይጠበቃል፡፡

በተጨማሪም ዴሞክራሲ በሂደት እንጂ በምኞት የማይገነባ በመሆኑ፣  በተፈጠረዉ ምቹ የፖለቲካ አዉድ፣ ካርድ በማውጣት በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ወሳኝ ተዋናይ የመሆን ፍላጎትን እና ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ያለንን ዝግጁነት በፖለቲካ ተሳትፎ ጥራት እዉን ማድረግ ዜጎች የሚወጡት ሃገራዊ ኃላፊነት ነው፡፡

ስለዚህ በሕዝብ ፈቃድ ላይ ጠንካራ ሀገረ መንግሥት በፅናት የሚቆመው "ሀገሬ በእኔ ድምፅ ትመራለች" የሚል ፅኑ እምነትን በተግባር ማሳየት ኢትዮጵያን እና ኢትዮጵያውያን የሚመጥን የስልጡን ዜጎች ማሳያ ነዉ እንላለን፡፡


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.