“የትንሳኤን በዓል ስናከብር የመልካምነት ተምሳሌ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

“የትንሳኤን በዓል ስናከብር የመልካምነት ተምሳሌት የሆኑ በጎ ሥራዎችን በመሥራትና በመተጋገዝ ሊሆን ይገባል”- ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ

የልደታ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የዘንድሮውን የትንሳኤ በዓል ምክንያት በማድረግ ከአቅመ ደካሞች ጋር በዓል አክብረዋል፡፡ 

በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዋና ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ በመርሀ ግብሩ ላይ ባደረጉት ንግግር የኢየሱስ ክርስቶስ የፍቅር መገለጫ የሆነው እና ሞትን ድል አድርጎ መነሳትን የሚያበስረው የትንሳኤ በዓል የመልካምነት መገለጫ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የትንሳኤ በዓልን ስናከብር የመልካምነት ተምሳሌት የሆኑ በጎ ሥራዎችን በመሥራትና በመተጋገዝ ሊሆን ይገባል ያሉት ዋና ሥራ አስኪያጁ የከተማ አስተዳደሩ ከአጋር አካላት ጋር በመተባበር ባቋቋማቸው የተስፋ ብርሃን የምገባ ማዕከላት በቋሚነት ከሚሰጠው የምገባ አገልግሎት በተጨማሪ አብሮነትን ለማጠናከርና በዓላቱን በደስታ እንዲያከብሩ በመደረግ ላይ እንደሚገኝ አክለው ገልፀዋል፡፡ 

የልደታ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ልዕልቲ ግደይ በበኩላቸው የትንሳኤን በዓል ስናከብር በአብሮነት፣ በመሰባሰብ፣ ያለንን በማካፈል እና ፍቅርን በመስጠት የቆየ ኢትዮጵያዊ እሴቶቻችንን በበለጠ በማጠናከር ሊሆን ይገባል ብለዋል፡፡ 

በተስፋ ብርሃን የምገባ ማዕከል ለበርካታ ወገኖች በቀን አንድ ጊዜ የምገባ አገልግሎት እንደሚሰጥ የተናገሩት ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ፣ ይህ ተግባር እንዲሳካ እንዲሁም በዓሉን አስመልክቶ የምሳ ግብዣውን በተሟላ ሁኔታ እንዲካሄድ ላደረጉ የከተማ፣ የክፍለ ከተማ እና የወረዳ አመራሮች እንዲሁም ልበ ቀና ተቋማትና ግለሰቦች ምስጋና አቅርበዋል፡፡


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.