ዛሬ በጉለሌ ክፍለ-ከተማ ተገኝተን 27ኛውን የተ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ዛሬ በጉለሌ ክፍለ-ከተማ ተገኝተን 27ኛውን የተስፉ ብርሃን የምገባ ማዕከል ስራ በማስጀመር ከማዕከሉ ተጠቃሚዎች ጋር የትንሳዔ በዓልን በጋራ አክብረናል።

በጉለሌ ክፍለከተማ ሶስተኛ ቅርንጫፍ የሆነውን ይህ 27ኛው የተስፉ ብርሃን የምገባ ማዕከል ስራ በማስጀመር፣ የምገባ ማዕከሉ ተጠቃሚ ከሆኑ ለማህበራዊ ችግር ከተጋለጡ ፣ አልባሽ አጉራሽ ለሌላቸው የሀገር ባለውለታ፣  ድጋፍ ለሚሹ ወገኖቻች ፣ ከአረጋዊያን እና ከአካል ጉዳተኞች ወገኖቻችንን እንኳን አደረሳችሁ ብለን በዓሉን በጋራ አክብረናል።

በዓሉ ጌታችን እየሱስ ክርስቶስ ያለአንዳች ልዩነት ለሰው ልጆች ሁሉ ራስን እስከ መስጠት ያሳየንን ፍቅር፣ በአብሮነት በፍቅና በመተሳሰብ ምሳሌነቱ በመከተል  ልንኖር እንደሚገባ  የሚስተምር በዓል ነው። 

እኛም በ28ቱም የተስፉ ብርሃን የምገባ ማዕከል በዚሁ በትንሳኤ በዓል ብቻ ሳይሆን ሁሌም ወገኖቻችን ስንመግብ ለዜጐቻችን ክብራችንና ፍቅራችንን የምንገልጥበትና ማህበራዊ ፍትህን የምናነግስበት ተግባር ነው። 
በዓሉን ምክንያት በማድረግ በሁሉም ክፍለ ከተሞች መዓድ የማቋደስ መርሐ-ግብር በማዕከላቱ እየተከናወኑ ይገኛሉ። 

“መስጠት አያጎድልም” በሚል መርሕ   የተደረገላቸዉን ጥሪ በመቀበል  የገነቡት በጎ ፈቃደኛ “የአዲስ ቪው ሆቴል ባለቤት አቶ አብይ አበራ” እና  በየቀኑ ለሚመመገብ የተረከበዉን “አኳስ ኮንስትራክሽን ፒ ኤል ሲ ባለቤት አቶ ወሰንን” በተጠቃሚዉ ወገን፣ በከተማ አስተዳደሩና በራሴ  ስም ምስጋናዬን አቀርባለሁ። 

በዓሉ የመተባበር፣ የመደጋገፍ እና የፍቅር በዓል ይሁንልን! መልካም በዓል። 

ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ!

ከንቲባ አዳነች አቤቤ


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.