“የሰንበት ገበያዎች በቅርበት በማግኘታችን ድካም...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

“የሰንበት ገበያዎች በቅርበት በማግኘታችን ድካም ቀንሶልናል፤ ገንዘባችንም ጊዜአችንም ቆጥቦልናል” ነዋሪዎች!

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ፣  የሰንበት ገበያዎች በተከተማዋ በሁሉም ክፍለ ከተሞችና ወረዳዎች ነዋሪው ባለበት መንደሮች ሁሉ፣ በቅርበት በመኖራቸው፣ ፍጆታዎችን ለመሸመት ይባክን የነበረውን ጊዜና ጉልበት ቀንሶልናል ሲሉ ምስክርነታቸውን እየሰጡ ይገኛሉ፡፡ 

በተለይም እነዚህ ገበያዎች በአቅራቢያቸው በማግኘታቸው የተለያዩ ምርቶችን ከአንድ ቦታ ሸምቶ ለመሄድ አስችሎልናል፣ ድካም ቀንሶልናል፣ የትራንስፖርት ወጪ አስቀርቶልናል፣ ከምንም በላይ ጥራት ያለው ምርቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ እንድናገኝ አስችሎናል ሲሉ ይደመጣሉ፡፡ 

መንግስትም ለኑሮ ውድነት መባባስ መንስኤ የሆኑትን የምርት አቅርቦት እጥረት ለመቅረፍ ፣ የፍጆታ እና የሰብል ምርቶች  በቀጥታ  ከአርሶ አደሮች እና ከባለሀብቶች ጋር በማስተሳሰር ምርት በከፍተኛ ሁኔታ ወደ ከተማ እንዲገባ  በማድረግ ሸማቹ ማህበረሰብ ፍትሃዊ ተጠቃሚ እንዲሆኑ በትኩረት እየሰራ ይገኛል፡፡

በዚህ ውጤታማ ስራ  ለዋጋ ንረትና ለንግድ ሚዛን መዛባት ምክንያት የሆኑ ህገ-ወጥ ነጋዴዎች እና ደላሎች ላይ ህጋዊ እርምጃዎችን በመውሰድ በገበያው ላይ ይታይ የነበረውን የዋጋ ንረት ማረጋጋት ተችሏል፡፡


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.