የዓለም-አቀፍ ኮንፈረሶች የስህበት ማዕከል፥ አዲ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

የዓለም-አቀፍ ኮንፈረሶች የስህበት ማዕከል፥ አዲስ አበባ!

አዲስ አበባ፥ የአፍሪካ የዲፕሎማሲ መዲና እና የዓለም-አቀፍ ስብሰባዎች ቀዳሚ መዳረሻ መሆኗን በተለያዩ ዘርፎች በተግባር እያረጋገጠች ትገኛለች። ከተማዋ ያላትን ጠንካራ የማስተናገድ አቅም፣ የሆቴል መሰረተ ልማት እና ልዩ የእንግዳ ተቀባይነት ባህል፣ ለበርካታ ታላላቅ ጉባኤዎች ተመራጭ እንድትሆን አስችሏታል።

መዲናችን ለኮንፈረንስ ቱሪዝም ተመራጭ እንድትሆን ካደረጓት ዋና ዋና ምክንያቶች፣  በከተማዋ ከ210 በላይ ኤምባሲዎች እና ቆንስላ ፅ/ቤቶች፣ ታላቁ የአፍሪካ ኅብረት እና የተባበሩት መንግሥታት የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን (UNECA) መቀመጫ መሆኗ እና በአጭር ጊዜ ያመጣችውን አስደማሚ የዕድገት መንገድ ተደምሮ ለአህጉራዊ እና ዓለም አቀፍ ውሳኔዎች ቁልፍ ስፍራ አድርጓታል።

በተለይ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ፥ ከተማዋ ለነዋሪዎቿም ሆነ ለጎብኚዎች ምቹ፣ ውብ እና ሳቢ ለማድረግ እየተከናወነ ያለው የኮሪደር ልማት ለዓለም አቀፍ ጉባኤዎች እና ጎብኚዎች ያላትን ተመራጭነት ይበልጥ አልቆታል።

በሌላ በኩል፥ ከተማዋን የቱሪዝም እና የኮንፈረንስ ማዕከል ለማድረግ የተገነባው “አዲስ ዓለም-አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል” ለከተማዋ ተጨማሪ የማስተናገድ አቅም የፈጠረ እና ለትላልቅ አለም አቀፍ ስብሰባዎችና ኤግዚቢሽኖችን ለማዘጋጀትም ዓቅም የፈጠረ ትልቅ ማሳያ ነው፡፡  

እንዲሁም “የዓድዋ ድል መታሰብያ ሙዝየም” ከታሪክና ቅርስ ማዕከልነቱ ባሻገር፣ በርካተ ስብሰባዎችን እና ኤግዚብሽኖችን በአንድ ጊዜ የማስተናገድ ማስተናገዱ ሌላው ለኮንፈረንስ ማዕከልነቷ ገፀ-በረከት ነው። 

በአጠቃላይ አዲስ አበባ፣ በታሪክ ብቻ ከመኖር በአሁናዊ መሬት ላይ በፈጠረችው አስደማሚ የዕድገት እና ሁለንተናዊ ከፍታ፣ “ከሀገራችን ዋና ከተማነት ባሻገር" የዓለምን ቀልብ እየሳበች፣ በፈጣን ለውጥ ላይ ያለች እና ለዓለም-አቀፍ ባለሀብቶች፣ እንዲሁም ለኮንፈረንስ ቱሪዝም ምቹ እየሆነች የመጣች ከተማ ናት።

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
  https://linktr.ee/addisababacommunication


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.