ማዕድ ያጋራ ቀዳሚ የለውጥ መንግስት:
የለውጡ መንግስት ወደ አስተዳደር ከመጣበት ጊዜ ጀምሮ በዓላት ሲከበሩ አዲስ አበባን ጨምሮ በመላው የሀገሪቱ አካባቢዎች የኢትዮጵያዊ አብሮነት መተሳሰብና ተካፍሎ መብላትን የሚያጎለብቱ እሴቶችን ተጠናክረው ቀጥለዋል፡፡
ማዕድ ማጋራት የሀገር ወዳድነት ምልክት ነው በሚል እሳቤ በለውጡ አመራሮች ተጀምሮ ከጊዜ ወደ ጊዜ ላለፉት 8 ተከታታይ ዓመታት በስፋት እየተተገበረ የሚገኝው ይህ በጎ ምግባር ፤ በበዓላት ወቅት በችግር ምክንያት ቤታቸውን ዘግተው የሚውሉ ዜጎች በዓላትን በደስታ እንዲያሳልፉና ሳቃቸው እንዲመለስ አስችሏል፡፡
ማዕድ ማጋራት መደጋገፍን፣ አንድነትንና መተሳሰብን የሚያጎላ መልካም እሴት ሲሆን የብዙዎችንም ሕይወት የታደገ በጎ ተግባር ነው:: እንዲህ አይነቱ ተግባር ተቀዛቅዞ የቆየውን የኢትዮጵያውያን የቆየ የመደጋገፍ ልምድ ያደስ ከመሆኑም በላይ ማጀታቸው የጎደለባቸው ዜጎች በዓሉን በደስታና በፍቅር እንዲያሳልፉ ከበጎ ልብ የተጠነሰሰ ከልባዊ ፍቅርና ርህራሄ በሚመነጭ ስሜት የሚከወን ነው !!
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/addisababacommunication
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.