ከመሸጋገሪያ ወደ ማዘወተሪያ የተቀየረችው አዲስ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ከመሸጋገሪያ ወደ ማዘወተሪያ የተቀየረችው አዲስ አበባ

ከተማችን አዲስ አበባ ደረጃቸውን የጠበቁ ውብ የመዝናኛ የማዘውተሪያ ስፍራዎችን መገንባቷ ለቱሪስቱ አዲስ እይታን  ለነዋሪው ደግሞ ውብ ማዘውተሪያን እያበረከተች ትገኛለች::

ይህ ደግሞ ከዚህ ቀደም ከተማዋ ወደሌሎች ሀገራት መተላለፊያ ብቻ አድርጓት የነበረውን ታሪክ በመቀየር መዳረሻ እሆነች እንድትመጣ አድርጓታል፡፡

ከታሪክና ከተፈጥሮ ባለፈ ወደ ልምድና መዳረሻ እየተቀየረች ያለችው ከተማችን የቱሪዝም ባለሙያዎች እንደሚናገሩት ለቱሪዝም መነቃቃት የመጀመሪያው የባህልና የታሪክ ሀብት በመሆኑ ከተማችን ይህንን በተግባር እየገለጠች ሲሆን በተጨማሪም የደህንነትና የሰላም ዋስትና  የመሰረተ ልማት ግንባታን በመገንባትና  በማረጋገጥ ለቱሪስቶች ቆይታቸውን ማራኪ በማድርግ እንዲያራዝሙ እያደረገች ነው፡፡

በከተማዋ የተገነቡት እንደ አንድነት እና እንጦጦ ፓርክ ያሉ ፕሮጀክቶች ከተማዋን አረንጓዴ ከማልበሳቸው ባለፈ፣ የቱሪስቶችን ቆይታ የሚያራዝሙና ለቤተሰብ ምቹ የሆኑ የገጽታ ግንባታ ውጤቶች ሆነዋል፡፡ 

በተጨማሪም እንደ የሳይንስ ሙዚየምና የታሪክ ማዕከላት  መገንባታቸው  የኢትዮጵያን ጥንታዊ ጥበብ ከዘመናዊ የቴክኖሎጂ ግስጋሴ ጋር በማጣመር፣ ለጎብኚዎች የተሟላ እውቀትና መዝናኛ የሚሰጡ ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ ስፍራዎች አድርጓቸዋል፡፡

ይህም ይህችን ውብ ከተማ በቱሪዝም እና በቱሪስት እንቅስቃሴ ከመሻጋገሪያ ወደ ማዘውተሪያ እየቀየራት መሆኑን እያስመሰከረች ነው፡፡

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
  https://linktr.ee/addisababacommunication


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.