"በመጪው ፋሲካ ለበዓል የሚሆኑ ግብአቶች እጥረት...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

"በመጪው ፋሲካ ለበዓል የሚሆኑ ግብአቶች እጥረት እንዳይኖር እና የኑሮ ውድነት እንዳይባባስ ከተማ አስተዳደሩ በትኩረት እየሰራ ነው"አቶ ጃንጥራር አባይ

የአዲስ አበባ ከተማ  ምክትል ከንቲባ እና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ  

ህብረተሰቡ መጭዉን የፋሲካ በዓል ያለምንም ችግር እንዲያሳልፍ እና የኑሮ ውድነት እንዳይባባስ ከተማ አስተዳደሩ በትኩረት እየሰራ እንደሆነ  የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ እና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ  አቶ ጃንጥራር አባይ  ገለጹ።

ምክትል ከንቲባ አቶ ጃንጥራር የኑሮ ውድነትን ለመቀነስ አና ገበያን ለማረጋጋት እንዲሁም  ለፋሲካ በዓልን የምርት አቅርቦትን በተመለከተ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።  

ለበዓል ዝግጅት የኑሮ ውድነቱ እንዳይባባስ የአደባባይ ባዛሮች እንደተከፈቱ እና ካለው የነዳጅ አቅርቦት ጋር የሚፈጠሩ የዋጋ ንረቶችን ለመከላከል እየተሰራ እንደሆነ አቶ ጃንጥራር ገልጸዋል ፡፡

ለበዓል የሚሆኑ ግብዓቶች የሰብል፣ የአትክልትና ፍራፍሬ ፣የእንስሳት ውጤቶች እና ሌሎች የፍጆታ ምርቶች ከሌሎች ክልሎች ጋር በመቀናጀት  በከተማችን ባሉ በማህበራት፣ የገበያ ማዕከላት፣ በሰንበት ገበያዎች እና በባዛርና ኤግዚቢሽኖች በስፋት እንዲገቡ  መደረጉንም አብራርተዋል፡፡

በተለይም ከተማ አስተዳደሩ አነስተኛ ገቢ ያለው ማህበረሰብ ተጠቃሚ  ለማድረግ  የሰንበት ገበያዎችን በቅርበት በማመቻቸት ምርት በስፋት እንዲገባ  በማድረግ እና የክትትልና ቁጥጥር ስራም እየተሰራ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

በከተማችን ከ242 በላይ የሰንበት ገበያዎች እንዳሉ የገለጹት ምክትል ከንቲባው አቶ ጃንጥራር  ምርት ለሚያስገቡ ተሸከርካሪዎች የነዳጅ አቅርቦት ቅድሚያ በመስጠት ምርት ወደ ከተማችን በስፋት እንዲገባ በማደረግ የሽንኩርትና መሰል የበዓል ምርቶች ዋጋ እንዳይንር መቻሉን ጠቁመዋል፡፡

በተጨማሪም ከ260 በላይ ስጋ መሸጫ የማህበራት ሱቆች እንዳሉና በእነዚህ ማህበራት የእርድ አቅርቦት እንደሚከናዎንም ገልጸዋል፡፡  

በዓላትን ምክንያት በማድረግ ህገወጥ የዋጋ ጭማሪ እንዳይኖር ተገቢው ቁጥጥር እንደሚደረግ እና የምርት አቅርቦት እጥረትም እንደማይፈጠር በእየ ደረጃው ባሉ መዋቅሮች ክትትል እንደሚደረግም አቶ ጃንጥራር አሳስበዋል፡፡


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.