ባለርዕይ መሪዎች የገነቧት-ውብ ከተማ፥ አዲስ አ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ባለርዕይ መሪዎች የገነቧት-ውብ ከተማ፥ አዲስ አበባ!

“አዲስ አበባ፥ የአፍሪካ የአብሮነት ህልምን እውን ያደረገች ከተማ”! 
በአፍሪካ ሀገሮች ጋዜጠኞች አንደበት!  

በቅርቡ በተካሄደው  የአፍሪካ ኅብረት የሚዲያ ፎረም ለመሳተፍ በመዲናችን የተገኙ ከሃያ ከሚበልጡ ሀገራት የመጡ ጋዜጠኞች፣ በከተማዋ የተሰሩ የወንዝ ዳርቻ ፕሮጀክት፣ የኮሪደር  ልማትና የተለያዩ የቱሪዝም መዳረሻዎችን ጎብኝቷል።

ጋዜጠኞቹ የአፍሪካ መዲና የሆነችው አዲስ አበባ፣  የደረሰችበትን ታላቅ ለውጥና ዕድገት በየሀገራቸው ቴሌቭዥን ጣቢያና ሌሎችም አማራጮች “የአፍሪካ የአብሮነት ህልምን እውን ያደረገች ከተማ” ብለው ገልጸዋል።

በጽሁፎቻቸው፥ በከተማዋ በአካባቢ ጥበቃና በመሰረተ ልማት የተሰሩ ስራዎች፣  ለአረንጓዴ አሻራ ትኩረት መሰጠቱ ፣ ከተማውን ንፁህ እና ለመኖር ምቹ ተስማሚ እንድትሆን  መደረጓ ትምህርት ሊቀሰምባት የሚገባ ከተማ መሆኗን ገልጸዋል።  

እንዲሁም  የእግረኞች፣ የብስክሌት መንገዶች፣ የስፖርት ማዘውተሪያዎች፣ የህፃናት የመጫወቻ ቦታዎች እና ለነዋሪዎች የማረፊያ ስፍራዎች መካተታቸው የአካባቢ ጥበቃንና የህዝብ ጤናን ከማሻሻል  ባለፈ ለቱሪዝም እድገት እንዲሁም የስራ እድልን ለማስገኘት ያለውን አስተዋጽኦ በዜና ትንታኔ አቅርበዋል።

አዲስ አበባ፥ የአፍሪካ የብልፅግና ተምሳሌት!

https://www.facebook.com/share/1Axx9xPzLC/?mibextid=wwXIfr


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.