በመዲናችን አዲስ አበባ መጪው የትንሳኤ በዓልን...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

በመዲናችን አዲስ አበባ መጪው የትንሳኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ የንግድና ባዛር መርሀ ግብር በዛሬው እለት በይፋ ተከፈተ

በመዲናችን በ11ዱም ክፍለ-ከተሞች መጪውን የትንሳኤ በዓል ምክንያት በማድረግ የንግድና ባዛር  መርሀ ግብር በዛሬው እለት በይፋ ተከፍቷል፡፡

ንግድና ባዛሩ የነዋሪውን የኑሮ ጫና ለማቃለል እና የገበያ ዋጋ ንረትን ለማረጋጋት ያለመ ይህም ከተማ አሰተዳደሩ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ ከሚሰራባቸዉ ተግባራት አንዱ እና ተጠናክሮ የቀጠለ ዉጤታማ ስራ ነዉ፡፡

በተጨማሪም ህብረተሰቡ በአቅራቢያው የበዓል መጠቀሚያ ምርቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲያገኝ የሚያስችል ሲሆን ህብረተሰቡን ካላስፈላጊ ወጪ ለማዳን በከተማዋ በአምስቱ የገበያ ማዕከላት ጭምር የግብርና እና የኢንዱስትሪ ምርቶች በስፋትና በጥራት እየቀረቡ ይገኛሉ፡፡

ነጋዴው ማህበረሰብ የተፈጠረለትን ምቹ ሁኔታ በመጠቀም ጥራት ያለዉ ምርት እንዲያቀርብ እና በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲሸጥ ሸማቹም አቅሙን ባገነዘበ መልክ በተዘረጋለት ፍትሃዊ የግብይት ስርዓት ተጠቃሚ እንዲሆን እንዲሁም  ህገ-ወጦችን ለመከላከል በሚደረገዉ ጥረት ሁሉም የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ ሲል ከተማ አስተዳደሩ ጥሪዉን አቅርቧል።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.