የኢትዮጵያ መንግሥት በInvest in Ethiopia 2026 ፎረም፤ ከቻይና፣ ፖላንድ፣ ህንድ፣ ሲንጋፖር እና ኬንያ ከመጡ አጋሮች ጋር የ13.1 ቢሊዮን ዶላር ታሪካዊ የኢንቨስትመንት ስምምነት ተፈራርሟል።
በታዳሽ ኃይል፣ በማዕድንና በአረንጓዴ አሞኒያ ዘርፎች ላይ ያተኮሩት እነዚህ ስምምነቶች የሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ አጀንዳችን ተጨባጭ ውጤት እያመጣ መሆኑን ጉልህ ማሳያ ናቸው። የውጭ ምንዛሬ ተመን ሊበራላይዜሽን፣ እና የባንክና ቴሌኮም ዘርፎችን ለንግድ ማህበረሰቡ ክፍት ማድረግ የመሳሰሉ ቆራጥ እርምጃዎች ግልጽና ምቹ የኢንቨስትመንት ከባቢ መፍጠራቸውን በተጨባጭ ያረጋግጣል። ይህም በዘመናዊ ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች እና በአፍሪካ አኅጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና አማካኝነት ለዓለም አቀፍ ገበያ ምቹ መዳረሻን ፈጥሯል።
ይህ ዕድገት በሁሉም ስትራቴጂካዊ ዘርፎች በግልጽ እየታየ የሚገኝ ሲሆን፤ በታላቁ የህዳሴ ግድብ የተንተራሰው የሀገራችንን የታዳሽ ኃይል ሀብትን በመጠቀም በሶላር ምርት እና በሃይድሮጅን ፕሮጀክቶች ላይ የተገኘው እመርታ፤ በሌላ በኩል ደግሞ የማዕድን ዘርፍ ምርታማነት በከፍተኛ ደረጃ እየተሰራበት ይገኛል። የኢንዱስትሪ ዕድገታችን አዲስ በሚገነቡት ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች እየተፋጠነ ሲሆን፣ የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ዘርፉም በዲጂታል ትራንስፎርሜሽን በልህቀት እየተመራ ይገኛል። በኢትዮጵያ አየር መንገድ ዓለም አቀፍ ትስስር እና በባህላዊ ቅርሶቻችን የታጀበችው ኢትዮጵያ ለዓለም አቀፍ ንግድና ቱሪዝም ተመራጭ መዳረሻ ሆናለች።
ዓለም አቀፍ ማህበረሰቡን ለላቀ አጋርነት እንጋብዛለን፤ ኢትዮጵያ ከነበረው እጅጉን በተሻለ ለንግድ ዝግጁ ናት!
#InvestInEthiopia #EthiopiaDelivers
#PMOEthiopia
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.