አረንጓዴ አሻራ፥ የዚህ ትውልድ ውጤት፤ የመጋቢት...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

አረንጓዴ አሻራ፥ የዚህ ትውልድ ውጤት፤ የመጋቢት ስኬት!

አረንጓዴ አሻራ በኢትዮጵያ፥ በ2011 ዓ.ም ጠቅላይ ሚኒስትር  ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ወደ ስልጣን ከመጡ በኃላ ካስመዘገቡት አኩሪ፥ በትውልድ ተዘካሪ ውጤት አንዱ ነው፡፡ ይህ ፕሮጀክት  ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የደን መጨፍጨፍ ለመከላከልና የአካባቢን የአየር ሁኔታ ለማሻሻል ብሎም የተራቆተውን መሬት አረንጓዴ በማልበስ  የምግብ ሉኣላዊነትን ለመረጋገጥና በተለይም  የአረንጓዴ ኢኮኖሚን በመገንባት ረገድ  ከፍተኛ አስተዋጾ እያበረከተ ይገኛል፡፡

ይህ ሀገራዊ ፕሮጀከት  የመሬት መራቆትን በመቀነስ፣ የአፈርና የውሃ ጥበቃ ሥራዎችን በማጠናከር የምግብና የውሃ ዋስትናን በማረጋገጥ፣ ኑሮን በማሻሻል እንዲሁም የአየር ንብረት ለውጥን የመቋቋም አቅምን በማሳደግ  የሀገሪቱን የወደፊት መልካም ዕጣ ፈንታ የሚያሳይ መሰረት እየጣለ ይገኛል፡፡

የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ሀገር በቀል እሳቤ ከመሆን ባለፈ ባለቤቱና ተጠቃሚው ህዝቡና ህዝቡ ብቻ በመሆኑ፣  በዚህም በርካታ የስራ ዕድል መፍጠር የተቻለ ሲሆን በተለይ ወጣቶችና ሴቶች ችግኝ በማፍላትና በመንከባከብ በስፋት ተጠቃሚ እየሆኑ ነው፡፡ አረንጓዴ አሻራ የተሻሻለ የግብርና አሰራር በማስፈን፣ የምግብ ዋስትናን በማረጋገጥ፣ የውሃ ሀብትንና የብዝሃ ህይወት ጥበቃን በማረጋገጥ ዘላቂ ተጠቃሚነትን ያስገኝ ነው።

በአረንጓዴ አሻራ ንቅናቄ በየዓመቱ በቢሊዮን የሚቆጠሩ ችግኞች ተተክለዋል። በዚህ ሀገራዊ ፕሮጀክት በተለያዩ አካባቢዎች የችግኝ ማፍያ ቦታዎች ተቋቁመው በስፋት እየሰሩ ናቸው ፤ማህበረሰቡን በማሳተፍ የችግኝ ተከላና እንክብካቤ ስራዎች በስፋት እየተከናወኑ ሲሆን በተለይም የአረንጓዴ አሻራ ፕሮጀክት በአገር ውስጥ ብቻ ሳይሆን በጎረቤት አገራትም ተስፋፍቶ መልካም ተሞክሮ በመሆን አርአያ መሆን ችሏል፡፡ 

አሁን ላይ ኢትዮጵያውያን  በየአመቱ አሻራቸውን ለማሳረፍ በጉጉት የሚጠባበቁት የአረንጓዴ አሻራ  መረሃ ግብር ዘመቻ የአገሪቱን  የአረንጓዴ እጽዋት ሽፋን ከማሳደግ በተጨማሪ  የአየር ንብረት ለውጥን  በመከላከል በሰዎች አኗኗር  ዘንድ ከፍተኛ ለውጥ እንዲኖር አድርገዋል፡፡

አረንጓዴ አሻራ፥ የዚህ ዘመን ትውልድ ውጤት ፤ የመጋቢት ስኬት!


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.