"የበርካቶችን ሸክም ያቀለሉ፣ የነገ ተስፋን ያበ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

"የበርካቶችን ሸክም ያቀለሉ፣ የነገ ተስፋን ያበሩ ሰው ተኮር የመጋቢት ፍሬዎች!"

መጋቢት 24 ቀን 2010 ዓ.ም፣ የለውጡ መንግስት ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር ያደረገበት ታሪካዊ ቀን ሲሆን መንግስት ሀገራዊ ኃላፊነቱን ከተረከበበት ጊዜ አንስቶ "ሰው ተኮር" ስራዎችን ዋነኛ መገለጫው በማድረግ፣ የዜጎችን ማህበራዊ፣ ስነ-ልቦናዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ለመቅረፍ ያለሙ ዘርፈ-ብዙ ተግባራትን እያከናወነ ይገኛል፡፡

ዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ዜጎችን ለመደገፍ፣ በበጋና ክረምት የሚከናወኑ የበጎ ፈቃድ ስራዎች ፤-የቤት ዕድሳት፣ የተስፋ ብርሀን ምገባ ማዕከላት ማስፋፋት፣ የተማሪዎች ምገባ ፕሮግራም፣ ማዕድ ማጋራት እና ሌሎች መሰል ተግባራትን ተቋማዊ በሆነ መልኩ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ የተሰራባቸዉ የበርካቶችን ሸክም ያቀለሉ፣ የነገ ተስፋን ያበሩ ሰው ተኮር የመጋቢት ፍሬ ዉጤቶች ናቸዉ፡፡

በተጨማሪም እንደ “የነገዋ” ያሉ የነገን ብሩህ ተስፋ የሚያሰንቁ የሴቶች የክህሎት ማበልፀጊያ እና የስነ-ልቦና ድጋፍ የሚሰጡ ማዕከላትን በመገንባት ሙያዊ ክህሎት በማስጨበጥ እና ወደ ስራ እንዲገቡ በማድረግ እህቶቻችን ነገአቸውን እንዲያልሙ በዚህም ተስፋቸው እንዲገለጥ እና እፎይታን እንዲጎናፀፉ ማድረግ መቻሉ ሌላዉ ማሳያ ነዉ፡፤
 
በሌላ በኩልም ከውጭ ለሚመጡ ስደተኞች ዜጋ ተኮር ፖሊሲ በመቅረፅ ህይወታቸዉ በአዲስ መልክ እንዲለወጥ፤የሃገር እና የወገን ኩራት ስሜት እንዲያድርባቸዉ በሚያስችላቸዉ ጉዳዮች ላይ ድጋፍ ማድረግ መጀመሩ መንግስት ለዜጎች ክብር የሰጠዉ መገለጫ  ነዉ ማለት ይቻላል፡፤

በአጠቃላይ እነዚህን በመሳሰሉት  እና ሰው ላይ ኢንቨስት የማድረግ ቀዳሚ ጉዳዮች ለሀገር የወደፊት ተስፋ መሰረት ነው በሚል እሳቤ  እየተከናወኑ የሚገኙ ሸክም አቅላይ፣ እፎይታ ሰጪ “ሰው ተኮር” ስራዎች ዛሬ ብቻ ሳይሆን ወደፊትም የበለጠ  ተጠናክረዉ የሚቀጥሉ  የመጋቢት ፍሬዎች እና አሳቤዎች ናቸዉ፡፡


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.