ዛሬ ማለዳ በምግብ ዋስትና እና ብቃት የወጣቶች...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ዛሬ ማለዳ በምግብ ዋስትና እና ብቃት የወጣቶች የሥራ ላይ ልምምድ ፕሮግራም 15 ሺህ 492 ተጠቃሚዎችን ከተረጂነት ወደ ምርታማነት በማሸጋገር አስመርቀናል።

ከተማችን አዲስ አበባ ለችግር የተጋለጡ ነዋሪዎችን ከተረጂነት ወደ ምርታማነት በማሸጋገር ረገድ ተጨባጭ ለውጥ እያስመዘገበች ትገኛለች። ይህ ተግባር በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ይፋ ከተደረጉት አምስቱ የ“ዜሮ ግቦች” መካከል አንዱና ዋነኛው የሆነው “ተረጂነትን እና ልመናን ዜሮ የማድረግ” ታላቅ ራዕይ በከተማችን ስኬታማ እየሆነ መምጣቱን ማሳያ ነው።

ባለፉት አምስት ዓመታት በሴፍትኔት ፕሮግራም ውስጥ ተይዘው ሲረዱ የነበሩ ከ695 ሺህ በላይ ነዋሪዎችን ወደ ምርታማነት በማሸጋገር ራሳቸውን እንዲችሉና ቤተሰቦቻቸውን እንዲደግፉ ተደርጓል።

በሌላ በኩል በከተማችን የሥራ ልምምድ ከተጀመረበት 2014 ዓ.ም ጀምሮ ዛሬ የተመረቁትን 8 ሺህ 852 ወጣቶች ጨምሮ 49 ሺህ የሚሆኑ ዜጎች ከተረጂነት እና ስራ አጥነት ወጥተው በተፈጠረላቸው ትስስር የሥራ ላይ ልምምድ አጠናቀው ወደ ስራ ባለቤትነት እና አምራችነት ተሸጋግረዋል።

ውድ የዛሬ ተመራቂዎች፤ ከተማችን እንደ እናንተ ዓይነት ትጉ፣ ያገኙትን ዕድል አሟጥጠው በመጠቀም ሕይወታቸውን በዘላቂነት የሚለውጡ እና ለሌላውም አርአያ የሚሆኑ ብርቱ ወጣቶች ያስፈልጓታል። በቀጣይም ከራሳችሁ አልፋችሁ ለሌሎች የሥራ ዕድል የምትፈጥሩ እና በሰነቃችሁት ራዕይ፣ ባካበታችሁት ልምድ የድርጅት ባለቤቶች ጭምር እንደምትሆኑ የእስካሁኑ ትጋታችሁ ትልቅ ማሳያ ነው፣ በርቱ !

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ሕዝቦቿን ይባርክ!

ከንቲባ አዳነች አቤቤ


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.