ታዋቂው ጥቁር አሜሪካዊ ራፐር ዲዲጂ የዓድዋ ድል...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ታዋቂው ጥቁር አሜሪካዊ ራፐር ዲዲጂ የዓድዋ ድል መታሰቢያን ጎበኘ

ዲዲጂ በሚል መጠሪያ የሚታወቀው ታዋቂው ጥቁር አሜሪካዊ ራፐር እና ዩቲዩበር ዳሪል ድዌይን ግራንቤሪ የዓድዋ ድል መታሰቢያን ዛሬ ጎብኝቷል፡፡ 

በጉብኝቱ በመታሰቢያው የሚገኙ ታሪካዊ ቅርሶችን እና የድሉን ወቅት የሚዘክሩ የጥበብ ስራዎችን ተዘዋውሮ ተመልክቷል። የኢትዮጵያን ቡና በሐገርኛ አቀራረብ ተስተናግዷል፡፡

ራፐሩ በኢትዮጵያ የዓድዋ ድል መታሰቢያን ጨምሮ በተለያዩ አካባቢዎች በመዘዋወር ጉብኝት እያደረገ እንደሚገኝ የዓድዋ ድል መታሰቢያ አስታውቋል።
ዲዲጂ እ ኤ አ በ2014 በዩቲዩብ እውቅናን በማግኘትና በ2018 ከኤፒክ ሬከርድስ ጋር በመፈራረም ወደ ሙዚቃው አለም ገብቷል፡፡ 

በማህበራዊ ሚዲያ ላይም ቀጥታ ስርጭት ፥ ስለ አኗኗር ዘይቤ፣ ከመድረክ ጀርባ ያሉ እና ሌሎችንም ተወዳጅ የሆኑ ኮንተንቶችን በማዘጋጀት በአሁኑ ሰዓት 4.3 ሚሊዮን የ ዩቲዩብ  እና 7.2 ሚሊዮን የቲክ ቶክ ተከታዮችን ያፈራ ዝነኛ ነው፡፡


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.