በህገ ወጥ መንገድ ከአዲስ አበባ ሊወጣ የነበረ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

በህገ ወጥ መንገድ ከአዲስ አበባ ሊወጣ የነበረ 6 በርሜል ነዳጅ ከነ ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር ማዋሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስታወቀ።

ተጠርጣሪዎቹ የወንጀል ድርጊቱን የፈጸሙት መሳለሚያ አካባቢ ከሚገኝ አንድ የነዳጅ ማደያ ሲሆን በማደያው በነዳጅ መቅዳት ሙያ ላይ የተሠማራው አሸናፊ ጥላሁን እና ሱልጣን ተክላይ የተባለ አሽከርካሪ ነው። 

ግለሠቦቹ ጨለማን ተገን በማድረግ ከተጠቀሰው የነዳጅ ማደያ የቀዱትን 6 በርሜል ወይም 1200 ሊትር ነዳጅ ኮድ 3 A 55857 አ/አ FSR ተሽከርካሪን በመጠቀም ጭነው ሲያዘዋውሩ በልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 5 ፔፕሲ አካባቢ በቁጥጥር ስር ሊውሉ መቻላቸውን የልደታ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል። 

ፖሊስ ተጠርጣሪዎቹን በቁጥጥር ስር በማዋል ባደረገው ምርመራም ነዳጁን በህገ ወጥ መንገድ ከከተማው ክልል ለማስወጣት ሲንቀሳቀሱ እንደነበርም ገልጿል። 

ወቅታዊውን ዓለማቀፉዊ ሁኔታ እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ወጥቶበት ወደ ሀገር ውስጥ የሚገባን የነዳጅ ምርት በህገ ወጥ መንገድ የሚያዘዋውሩ፣ ነዳጅ የሚደብቁና መሠል የወንጀል ድርጊት ውስጥ በሚገቡ የነዳጅ ማደያዎች፣ ሠራተኞችና ግለሠቦች ላይ የሚወስደውን ህጋዊ እርምጃ አጠናክሮ እንደሚቀጥል የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አሳስቧል።
*
ዘገባ፦ ሳጅን ፍፁም በቀለ 
Addis Ababa Police


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.