"አዲስ አበባ ለአፍሪካዉያን ብሎም ለቀሪዉ ክፍለ ዓለማት ላሉ ጥቁር ህዝቦች ኩራት የሆነች ዉብ እና ድንቅ ከተማ ነች ።"ጎብኚዎች
የአፍሪካ የሚዲያ ባለሙያዎች ቡድን በአዲስ አበባ የተገነቡ የልማት ስራዎችን ጉበኙ
ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የተወጣጡ የሚዲያ አካላት ቡድን በአዲስ አበባ የተገነቡ ግዙፍ የልማት ስራዎችን ጎብኝተዋል።
በዛሬው እለት የተካሄደው የጉብኝት መረሃ ግብር በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮሙኒኬሽን ቢሮ እና በአፍሪካ ህብረት ትብብር የተዘጋጀ ነው።
የሚዲያ ባለሞያዎቹ በከተማዋ የተከናወኑ እና እየተከናወኑ ያሉ ዘርፈ ብዙ አገልግሎት ያላቸዉን የተለያዩ ሜጋ ፕሮጀክቶችን እንቅስቃሴ በጎበኙበት ወቅት እንደተናገሩት በከተማዋ የታየው ፈጣን ለውጥና የልማት ተነሳሽነት ለአፍሪካዉያን ብሎም ለቀሪዉ ክፍለ ዓለማት ላሉ ጥቁር ህዝቦች ኩራት የሆነች ዉብ እና ድንቅ ከተማ መሆኗን ገልፀዋል።
አክለዉም መዲናዋ ያላትን ገናና ታሪክ እና የተጣለባትን ታሪካዊ ኃላፊነት በዘላቂነት እየተወጣች መሆኗን ገልፀዉ ያዩትን ተጨባጭ የከተማዋን ሁለተናዊ ፈጣን እድገት ለሌሎች በማጋራት የሙያ ኃላፊነታቸዉን እንደሚወጡም ተናግረዋል።
በመጨረሻም ከተማ አስተዳደሩ ባደረገለቸዉ መልካም ትብብር እና የአዲስ አበባ ከተማ ቱሪዝም ቢሮ ባስጎበኘበት ወቅት ባሳየዉ የላቀ ትጋት ጎብኚዎቹ ምስጋናቸዉን አቅርበዋል።
የልዑካን ቡድኑ የወንዝ ዳርቻ ልማት እና የካሳንቺስ መልሶ ማልማት ስራዎችን፣ ከቦሌ - ሲኤምሲ እና ከመገናኛ - ሲኤምሲ የተከናወኑ የኮሪደር ልማት ስራዎችን፣ ከአራት ኪሎ - ፒያሳ የመንገድ እና የጉለሌ የተቀናጀ ልማት ስራዎችን እንዲሁም የአዲስ አፍሪካ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ማዕከል መጎብኘታቸዉ ታዉቋል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.