ዛሬ የሀገር ባለውለታና የብሔራዊ ኩራታችን ምንጭ ለነበሩ ለአንዳንዳ ማህበራዊ ችግር ለተጋለጡ አንጋፋና ጀግኖች አትሌቶቻችን ድጋፍ አድርገናል ።
እነዚህ አትሌቶች አገራችን በአለም አትሌቲክስ መድረክ መሳተፍ ከጀመረችበት ጊዜ አንስቶ ለራሳቸዉ ገንዘብ ከመስራት ይልቅ በታላቅ የሀገር ፍቅር የኢትዮጵያን ስምና ሰንደቅ ዓላማ በዓለም አደባባይ ከፍ አድርገው ያወለበለቡ ናቸው።
በአሁኑ ወቅት በእድሜ፣ በጤናና በተለያዩ ችግሮች ውስጥ የሚገኙ ጀግኖቻችንን ከኢትዮጵያ አንጋፋ አትሌቶች ማህበር ጋር በመተባበር በመለየት ድጋፍ አድርገናል፦
በዚህም መሰረት
1- ለአትሌት ኮማንደር ጌጤ ኡርጌ፦ 10 ሚሊዮን ብር፣ ባለ 3 መኝታ የመኖሪያ ቤት ከሙሉ የቤት እቃ ጋር፣ እንዲሁም አትሌቷ ካለችበት የጤና ሁኔታ አንፃር በጤና ቀጣይ ህክምና ድጋፍ እንድታገኝ ፣
2-ለአንጋፋ አትሌት ዋሚ ቢራቱ፣
3 -ለአንጋፋ አትሌት አጥሬ በዛብህ፣
4- ለአንጋፋ አትሌት ሸዋንግዛው ወርቁ፣ 5- ለአንጋፋ አትሌት ወርቁ በሮ፣
6- ለአንጋፋ አትሌት ግርማ ወ/ሃና፣
7- ለአንጋፋ አትሌት ሸምሱ ሀሰን፣
8- ለአንጋፋ አትሌት ሻይቱ ሽፈራው፣
9- ለአንጋፋ አትሌት ዘውዴ ሀ/ማሪያም፣ 10 ለአንጋፋ አትሌት ጌታቸው ከበደ እና 11- ለአንጋፋ አትሌት ወልዴ ሮባሌ ለእያንዳንዳቸው የ2 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አድርገናል ።
ለዚህ መልካም ተግባር ጥሪ ስናደርግላቸዉ በደስታ ተቀብለው፣ እንደ ሁልጊዜውም ካላቸው ቆርሰው ለሰጡን ሀገር ወዳድና ልበ ቀና ባለሀብቶች ድጋፍ በተደረገላቸዉ አንጋፉ አትሌቶች ስም ከልብ የመነጨ ምስጋናዬን አቀርባለሁ።
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.