ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ልዑካቸው የ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ልዑካቸው የአዘርባጃን የሕዝብ አገልግሎት እና ማኅበራዊ ፈጠራ የመንግሥት ኤጀንሲ (ASAN) የፈጠራ ማዕከልን ጎብኝተዋል።

ጉብኝቱ አዘርባጃን በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) የሚመራ አስተዳደርን ለማስፋፋት እና የሕዝብ አገልግሎቶችን በዲጂታል ለማዘመን የምትከተለውን ስትራቴጂያዊ አካሄድ የሚያሳይ ነው። በተጨማሪም በሀገሪቱ የ AI ኢንጂነሪንግ እና የአመራር ሥልጠና ዋና ማዕከል የሆነውን የ AI አካዳሚን ተዘዋውረው ተመልክተዋል።

‎ልዑኩ ጉብኝቱን በመቀጠል በክልሉ ውስጥ ካሉ ትላልቅ የነዳጅ እና የጋዝ ማቀነባበሪያ ማዕከላት አንዱ ወደሆነው ሳንጋቻል ተርሚናል እና ወደ አላት ነፃ የኢኮኖሚ ቀጣና አምርቷል። እነዚህ ጉብኝቶች በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የንግድ፣ የኢነርጂ እና የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ትብብር ይበልጥ የማጠናከር አቅም አላቸው። 

#PMOEthiopia 
 
 ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
  https://linktr.ee/addisababacommunication


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.