እንኳን ለመላው ጥቁር ሕዝቦች ኩራት ለሆነው የአ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

እንኳን ለመላው ጥቁር ሕዝቦች ኩራት ለሆነው የአድዋ ድል መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

ከአንድ ምዕተ ዓመት በላይ ተዳፍኖ የቆየው የአድዋ ድል ዳግም በኩራት እንዲያንሰራራ ያስቻለውና ታላቁ የአድዋ ድል መታሰቢያ የዘንድሮዉን የአድዋ ድል  ከመከላከያ ሠራዊት ፣ ከባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር፣ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ የከተማችን ነዋሪዎች በተገኙበት ዛሬ ማለዳ በታላቅ ድምቀት ተከብሯል።

ትናንት በደማቸውና በአጥንታቸው የሀገርን ዳር ድንበር ያስከበሩ፣ ሕዝባቸውንም በክብር ያኖሩ ጀግኖች መታሰቢያ በሆነው በዚህ ስፍራ፤ የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ጋር በመሆን የአድዋን 130ኛ ዓመት እንደ ስሟ አበባ በሆነችው አዲስ አበባ በታላቅ የማስ ስፓርት አክብረነዋል።

በድጋሚ እንኳን አደረሳችሁ!
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ! 
 
ከንቲባ አዳነች አቤቤ


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.