ኢትዮጵያ በትውልድ ቅብብሎሽ ሀገር ያጸኑ የበርካታ ጀግኖች ምድር ናት።
የመከላከያ ሠራዊት የልዩ ዘመቻዎች እዝም ባለፉት 65 ዓመታት በበርካታ ፈተናዎች ውስጥ የማይበገር ጽናት ይዞ ኢትዮጵያን ያኮራ ጀብዱ ፈጽሟል። እዙ አሁን ላይ በመከላከያ ሪፎርም ስራዎች አማካኝነት አየር ወለድ፣ ኮማንዶ እና ልዩ የጸረ ሽብር ኃይል በመያዝ በአደረጃጀት፣በሠው ኃይል እና በትጥቅ ዘመኑን በዋጀ መልኩ ተዋቅሮ በየትኛውም ጊዜና በማንኛውም ሁኔታ ግዳጁን በብቃት ለመፈጸም በአስተማማኝ ቁመና ላይ ይገኛል።
እዙ 65ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን ሲያከብር የገነባውን የዘመነ ወታደራዊ አቅም፣ የሰው ኃይል ዝግጁነት እና የታክቲክ ብቃት ለሕዝብ ይፋ አድርጓል። በተለይም ዛሬ የቀረበው የተቀናጀ የውሃ ላይ ልምምድ ፣ የአየር ወለድና የኮማንዶ አባላት በቅንጅት ያሳዩት ልዩ ልዩ ወታደራዊ ክህሎት የሠራዊቱን ከፍተኛ ብቃት ያረጋገጠ ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.