በ 24/7 የሥራ ባህል የዓለም የዲፕሎማሲ ማዕከል የሆነችውን አዲስ አበባን፤ ይበልጥ ፅዱ፣ ውብ፣ ሰላማዊና የዓለም የቱሪስት መዳረሻ በማድረግ ረገድ ትልቅ አሻራ ላኖራችሁ ተቋማት የላቀ ምስጋናችንን አቀርባለሁ።ከንቲባ አዳነች አቤቤ
አዲስ አበባ ታመሰግናለች!
አሁን ላይ አዲስ አበባችን በሰላማዊነቷና በዘላቂ ልማቷ ብዙዎች የሚደነቁባት ከተማ ሆናለች። ይህም በተለወጠ የሥራ ባህል ከመላው ሕዝባችን ጋር በመሆን በሠራነው ሥራ የተገኘ ውጤት ነው።
የዘንድሮው 39ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ፣ እንዲሁም የጣሊያን-አፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ ከወትሮው በተለየ እጅግ በተዋጣለትና ታሪካዊ በሆነ መንገድ እንዲጠናቀቅ አስተዋጽኦ ላደረጉ ተቋሟቻችን እና የከተማችን ነዋሪዎች የምስጋናና የዕውቅና መርሐ ግብር፤ ዛሬ ማምሻውን ውብ ሆኖ በተገነባው የካዛንቺስ በቡና ፕላዛ አካሂደናል።
መላው የከተማችን ነዋሪዎችን ጨምሮ፤ አመራሮች፣ ሠራተኞች፣ ተቋማት፣ የከተማና የፌዴራል የፀጥታ ኃይሎች በቅንጅት ለሠራችሁት አስደናቂ ሥራ ከልብ አመሰግናለሁ። በተለይም በዑራኤል - ቦሌ ብራስ የኮሪደር ልማት ሥራ ላይ የተሳተፋችሁና ያስተባበራችሁ አመራሮች፣ ሠራተኞችና ተቋማት፣ እንዲሁም ለሥራው ቀና ትብብር ያደረጋችሁ ባለሀብቶች በሙሉ፤ በራሴና በከተማው አስተዳደር ስም ከልብ አመሰግናለሁ።
አዲስ አበባ ምንጊዜም ታመሰግናችኋለች !
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ሕዝቦቿን ይባርክ!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.