ዛሬ የብልፅግና ፓርቲያችንን የ7ኛው አገራዊና ከ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ዛሬ የብልፅግና ፓርቲያችንን የ7ኛው አገራዊና ከተማ አቀፍ ጠቅላላ ምርጫ ማኒፌስቶን እና የምርጫ ምልክታችን የሆነውን "የስንዴ ነዶ" በአዲስ አበባ ደረጃ ይፋ አድርገናል።

ምርጫ ለአንድ አገር ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ መሠረታዊ ነው። የሕዝብ ሉዓላዊነት የሚገለጽበትና ሕዝብ በድምፁ መንግሥት የሚመሠርትበትም ሂደት ነው። 
በመሆኑም በ6ኛው አገራዊ ምርጫ ለሕዝባችን የገባነውን ቃል፣ ሕዝባችንን ከጎናችን በማሰለፍ በብቃትና በውጤት ፈጽመናል። በ7ኛው ዙርም ለሕዝባችን ቃል የምንገባው፣ ከተመረጥን ያለምነውን ሁለንተናዊ ብልፅግና ሌት ተቀን በመሥራት ያለምንም መሸራረፍ እንደምንፈጽም ነው።

የብልፅግና ፓርቲ ማኒፌስቶ ትናንትን ማከሚያ፣ ዛሬን በአግባቡ መጠቀሚያ፣ ነገን መተለሚያና ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት አገር ማሻገሪያ መመሪያችን ነው። 
የምርጫ መወዳደሪያ ምልክታችን የሆነው የስንዴ ነዶም የመደመር፣ የአንድነት፣ የተባብሮ መሥራት፣ የምርታማነት፣ የተምሳሌትነት፣ የልዕልና እና የሉዓላዊነት መገለጫ ነው። ይህም በሁላችን፣ ከሁላችን፣ ለሁላችን ብልፅግናን የምናረጋግጥበት ምልክታችን ነው።
ስለሆነም፣ ብልፅግና ቃሉን ይጠብቃል፤ ቃሉን ይፈጽማል፤ ሕዝቡን የሉዓላዊ ሥልጣን ባለቤት ያደርጋል!

ብልፅግናን ይምረጡ!
ኢትዮዽያን ወደ ተምሳሌት አገር !

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ሕዝቦቿን ይባርክ !! 
 
 
 ከንቲባ አዳነች አቤቤ

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
  https://linktr.ee/addisababacommunication


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.