ዛሬ በ24/7 የሥራ ባሕል የከተማችንን የኮሪደር...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ዛሬ በ24/7 የሥራ ባሕል የከተማችንን የኮሪደር ልማት ሥራዎች እያፋጠኑ ከሚገኙ ታታሪ ሰራተኞች ጋር ማዕድ በማጋራት አበረታተናል።

እነዚህ ብርቱ ሰራተኞች  በተለያዩ የግንባታ ሳይቶች፤ በተለይም በካዛንቺስ የሕፃናት ዓለም፣ በስፖርት ፓርክ እና በአዲስ አኳሪየም ግንባታዎች፣ እንዲሁም ከኡራኤል እስከ ቦሌ ቪ.አይ.ፒ (VIP)፣ ከኢንግሊዝ ኢምባሲ 22  እስከ ቦሌ ፍሬንድሺፕ ሆቴል እና ከውኃ ልማት እስከ ቦሌ ሩዋንዳ አካባቢ እየተከናወኑ ባሉ መጠነ ሰፊ የኮሪደር ልማት አያያዥ መስመሮች ላይ ሌት ተቀን የሚተጉ ናቸው።

በከፍተኛ የአገር ፍቅር ስሜት ለከተማችን ሁለንተናዊ ዕድገት በእውቀታቸውና በጉልበታቸው እያበረከቱ ላለው አስተዋፅኦ ከልብ እናመሰግናለን፤ አዲስ አበባ ሁልጊዜም ታመሰግናችኋለች።
በከተማችሁ መልማት በመደሰት ሁሌ በማዕድ ማጋራት እና  እነዚህን ብርቱ ሰራተኞ  በማበረታት መርሃ ግብር እየተሳተፋችሁ ላላችሁ  ባለሀብቶች  በራሴና በከተማ አስተዳደሩ ስም ምስጋናዬን አቀርባለሁ።

ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ!

ከንቲባ አዳነች አቤቤ


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.