የኮሪደር እና ወንዝ ዳርቻ ልማት አፈፃጸምን በተመለከተ
👉ባለፉት 6 ወራት ከኮሪደር እና ወንዝ ዳርቻ ልማት በተሰሩ ስራዎች ፤- ከአራት ኪሎ - ሽሮ ሜዳ ኮሪደር ፣ የሳውዝጌት-መገናኛ - መስቀል አደባባይ ኮሪደር፣ የሳርቤት- ካርል አደባባይ - አቦ ማዞሪያ - ላፍቶ አደባባይ - ፉሪ ኮሪደር፣ የሲኤምሲ - ሰሚት - ጎሮ - ቦሌ ቪአይፒ ኮሪደር ተጠናቀው ለህዝብ አገልግሎት ክፍት ተደርጓል፡፡
👉3ሺህ ሄክታር መሬትና 48 ኪ.ሜ ሜትር ዝርመት የሚሸፍኑ 8 የወንዝ ዳርቻ ልማቶች እየተከናወኑ ሲሆን፤ በተለይም 25 ኪ.ሜ በላይ የሚሸፍነው የእንጦጦ ፒኮክ-ካራማራ ድልድይ፣ 2ዐ ኪ.ሜ የሚሸፍነው የቀበና ግንፍሌ እንዲሁም ቁርጡሚ ወንዝ ዳርቻ እጅግ ውብ፣ ጤናማና የቱሪስት መዳረሻ በሚሆን መልኩ ስራወ በፍጥነትና በጥራት 24/7 በመስራት በመጠናቀቅ ላይ ይገኛሉ፡፡
👉የተሰሩትን ቁልፍ የሆኑ መሰረታዊ ልማቶች ከማስቀጠል አንፃር መዋቅር በማዘጋጀት የኮሪደርና ወንዝ ዳርቻ ልማት ባለስልጣን ተቋቁሞ ወደ ስራ የተገባውም በዚሁ ግማሽ አመት ነው::
👉ከኡራኤል - አትላስ - ቦሌ ብራስ፣ ከጎላጎል - ኤድናሞል - ፍሬንድሺፕ እና ከውሃ ልማት በአትላስ ሩዋንዳ ድልድይ ኮሪደር ልማት ስራ በመጠናቀቅ ላይ ይገኛል፡፡
👉አራዳ ፓርክ፣ አራት ኪሎ መኪና ማቆያና የገበያ ማእከል፣ የአራዳ የመኪና ማቆሚያ እና የገበያ ማዕከል እንዲሁም የመኪና ማቆሚያና የድል ፕላዛ ተጠናቀው ለአገልግሎት ዝግጁ ሆነዋል፡፡
👉ከነዚህ በተጨማሪ ከመደበኛ እቅዶች በተጨማሪ በኮሪደር ልማት 17 ኪሎ ሜትር የአስፋልት መንገድ፣ 34 ኪሎ ሜትር የእግራኛ መንገድ፣ 13 የመኪና ማቆሚያ ቦታዎች በመጠናቀቅ ላይ ናቸው፡፡
👉በከተማ ደረጃ ከሚሰራው መጠነ ሰፊ የኮሪደር ልማት በተጨማሪ በክፍለ ከተሞች አቅም በአራዳ፣ በንፋስ ስልክ ላፍቶ፣ በለሚ ኩራ እና በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተሞችም ተጀምረዋል፡፡
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.