መጪውን የገና በዓል ምክንያት በማድረግ የግብርናና የኢንዱስትሪ ምርቶች በተመጣጣኝ ዋጋ መቅረባቸው ተገለፀ።
የዋጋ ንረትን ለመቀነስ በከተማው በሚገኙ ሁሉም የባዛርና ሰንበት ገበያዎች እንዲሁም በገብያ ማእከላቶች ላይ የግብርና እና የኢንዱስትሪ ምርቶች በተመጣጣኝ ዋጋ እየቀረቡ መሆኑን ተገልጿል።
እንዲከናወኑም እስከ ታችኛው የገበያ ሰንሰለት ድረስ ግብረ ሃይል ተቋቁሞ አስፈላጊው ቁጥጥር እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የምርት አቅርቦት እጥረት እና ስርጭት ችግር እንዳይፈጠር በክፍለ ከተማው የተቋቋመው የገበያ ማረጋጋት ግብረ ሀይል በምርት አቅርቦትና በዋጋ ቁጥጥር በስፋት እየተሰራ መሆኑንም ግብረ ሃይሉ አስታውቋል።
ለከተማው ነዋሪዎች ለበዓሉ አስፈላጊ የሆኑ የግብርና እና የፋብሪካ ምርቶች በመንግስት የገበያ ማዕከላት፣ በቅዳሜና እሁድ እንዲሁም ለበዓሉ በተዘጋጁ ባዛሮች በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲቀርቡ መደረጉን ነው የተገለጸው።
በእነዚህ የገበያ ማዕከላት እየቀረቡ ከሚገኙት ምርቶች መካከል የዳልጋ ከብት፣ በግ፣ ፍየል፣ ዶሮ፣ እንቁላል እንዲሁም የዘይት ምርት፣ የሰብል ምርቶች፣ አትክልትና ፍራፍሬ ናቸው ተብሏል።
መጪውን የገና በዓል ምክንያት በማድረግ ለበዓሉ የሚያስፈልጉ ግብዓቶች በገበያዎች የቀረቡ ሲሆን፣ ኅብረተሰቡም በአቅራቢያው በሚገኙ ገበያዎች ምርቶቹን ነዋሪው በአቅራቢያው በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲሸምት ጥሪውም አቅርቧል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.