በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የ2018 የገና...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የ2018 የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ ለቀናት የሚቆይ ኤግዚቢሽንና ባዛር ተከፍቷል።

ባዛሩም የንግድ፣ የስራና ክህሎት፣ የኢንዱስትሪ ልማት፣ የህብረት ስራ ማህበራት፣ የባህልና ኪነ-ጥበብ እንዲሁም የአርሶአደርና ከተማ ግብርና ጽ/ቤቶች በጋራ የተዘጋጀ ነው።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የስራና ክህሎት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ዳግማዊት ግርማ በመክፈቻ ስነ-ስርዓቱ ላይ 6ቱ ተቋማት ተቀናጅተው የንግድ ባዛሩን ማዘጋጀታቸው የግብርናና የኢንዱስትሪ ምርቶች በበቂ፣ በጥራትና በተመጣጣኝ ዋጋ ለህብረተሰቡ እንዲዳረስ በማድረግ ረገድ ጉልህ ሚና እንዳለው ተናግረዋል።

በከተማችን የኑሮ ውድነትን ለማረጋጋት የደላላ ሰንሰለቶችን በመበጣጠስ ሸማችና አምራቹን በቀጥታ የሚያገናኝ ስርዓት መዘርጋቱን የጠቆሙት ኃላፊዋ ህብረተሰቡ ካላስፈላጊ ወጪ ራሳቸውን ለመጠበቅ የንግድ ባዛሮች ላይ እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርበዋል። 

የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ ወይዘሮ ካባ መብራቱ፣ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት በማስተላለፍ የኑሮ ውድነትን በመቀነስና ገበያ በማረጋጋት ረገድ የቅዳሜና እሁድ ገበያዎች እንዲሁም የላፍቶ አትክልት ገበያ ትልቁን ሚና እየተጫወቱ መሆኑን ጠቁመው ህብረተሰቡን ተጠቃሚ በማድረግ ረገድ በርካታ ስራዎች መሰራታቸውን ተናግረዋል።

ለ5 ቀናት በሚቆየው የባዛር ዝግጅት ላይም ለበዓል የሚያስፈልጉ ሁሉም ምርቶች በበቂ ሁኔታ መዘጋጀታቸውን የጠቆሙት ዋና ስራ አስፈፃሚዋ ህብረተሰቡ በተረጋጋ ሁኔታ ግብይታቸውን እንዲፈፅሙ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

አምራች ኢንተርፕራይዞችና የምርት አቅራቢዎች በበኩላቸው ባዛሩ ምርቶቻቸውን ለማስተዋወቅና የገበያ ትስስር ከመፍጠር አኳያ ጉልህ አስተዋፆ እንዳለው ገልፀዋል።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.