በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የገና በዓል ኤግዚቢሽንና...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የገና በዓል ኤግዚቢሽንና ባዛር ተከፈተ፡፡

የምርታማነት እምርታ ለዘላቂ ከፍታ” በሚል መሪ ሀሳብ የገና በዓል ኤግዚቢሽንና ባዛር በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ተከፍቷል።

ባዛሮች አምራቾችን ከሸማቾች ጋር በማገናኘት የገበያ ትስስር በመፍጠር ገበያን የሚያረጋጉ፣ምርቶቻቸውን ለማስተዋወቅ ዕድል የሚፈጥሩ መሆናቸውን ተገልጻል፡፡

ባዛሩን በይፋ የከፈቱት በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ስራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሚሊዮን ማቴዎስ እንደገለፁት በተለያዩ ወቅቶች የሚከፈቱት ባዛሮች አምራቾችን ከሸማቾች ጋር ቀጥታ በማገናኘት አምራቹን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ናቸው ብለዋል፡፡ 

ምርቶችን ከአርሶ አደሩ ቀጥታ ወደ ገበያ በማቅረብ በዓልን ተከትሎ አላስፈላጊ የዋጋ ጭማሪ እንዳይከሰት በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ አቶ ሚሊዮን ማቴዎስ ገልፀዋል።

እነዚህ ኤግዚቢሽንና ባዛር ገበያን በማረጋጋት የኑሮ ውድነት ጫናውን የማቅለልና በበዓላት ወቅት ህብረተሰቡ ምርቶችን በአቅራቢያው በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲያገኙ የጎላ ሚና እንዳላቸውም አቶ ሚሊዮን ማቴዎስ ተናግረዋል።

ኤግዚቢሽንና ባዛሩ ከዛሬ ታህሳስ 24 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ በዓሉ ዋዜማ እንዲሚቆይ ተገልጿል።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.