አዲስ አበባን በአፍሪካ ለሕፃናት ማሳደግ ምቹና...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

አዲስ አበባን በአፍሪካ ለሕፃናት ማሳደግ ምቹና ተመራጭ ከተማ ለማድረግ የጀመርነው ሥራ ፍሬ እያፈራ ይገኛል።

በከተማችን እየተተገበረ ባለው የቀዳማይ ልጅነት ልማት መርሃ ግብር አማካኝነት፣ በየሰፈሩ የለየናቸው ውስብስብ እና ከፍተኛ የአካል ጉዳት ያለባቸው 177 ሕፃናት እንደየጉዳታቸው ሁኔታ የተዘጋጁ ምቹ ዊልቸሮች ድጋፍ ተደርጎላቸዋል።

ዊልቸሮቹ  እንደየሕፃናቱ የአካል ጉዳት ሁኔታ ተስማሚ ሆነው መሠራታቸው ለሕፃናቱ ምቹና ውጤታማ ድጋፍ እንዲሰጡ ያደርጋቸዋል። ይህም የአካታችና ሁሉን አቀፍ ልማታችን አካል ሲሆን፣ ከተማችን ማህበራዊ ፍትህ የነገሰባት ትሆን ዘንድ በቀጣይ ተደራሽ ያልሆኑ ሕፃናትን ተጠቃሚ ለማድረግ በቁርጠኝነት እንሰራለን።

ይህንን በጎ ተግባር ያስተባበራችሁና አብራችሁን በቅርበት እየሠራችሁ ያላችሁ አጋሮቻችንን፣ በተለይም የክሊንተን ሄልዝ አክሰስ ኢኒሼቲቭን በተጠቃሚ ሕፃናትና ወላጆቻቸው ስም ከልብ አመሰግናለሁ።

ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ!

ከንቲባ አዳነች አቤቤ


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.