የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት፡-

ሀሳብ የለውጥ ኃይል ነው። ምሁራን ደግሞ የለውጥ ወኪሎች ናቸው። ምሁራን በማኀበረሰብ ውስጥ የሚፈጥሩት ለውጥም ሀገርን ወደ ብልጽግና ይወስዳል። በመሆኑም ምሁራን ሀሳብ አክባሪና አፍቃሪ፣ ጥልቅ አሰላሳይ፣ አንባቢ፣ ችግር ፈቺና መፍትሄ አሳሽ መሆን ይጠበቅባቸዋል።

በዛሬው እለት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ 75ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን በማስመልከት ዩኒቨርሲቲው ባዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ ጽሁፍ በማቅረብ ተሳትፍያለው። በመድረኩም የኢትዮጵያ ምሁራን በሁለንተናዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ያላቸውን ሚና በሚመለከት ሰፊ ውይይት አድርገናል።

የመደመር መንግስት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በሀገራዊ የብልጽግና ጉዞ ላይ አይተኬ ሚና እንዳላቸው በጽኑ ያምናል፣ ለተግባራዊነቱም እየሰራ ይገኛል። ተቋማቱም የመማር ማስተማር እንዲሁም የምርምር ስራዎችን ከቴክኖሎጂ ጋር በማናበብ ወደ ፈጠራና ተግባር መለወጥ ይጠበቅባቸዋል። ይህም የኢትዮጵያን ብልጽግና በተደመረ አቅም ለማፋጠን ሚናው ከፍተኛ ነው።

ይኽን ትውልድን በዐዲስ ብርሃን ነው የምመለከተው። ተስፋ ይሰጠኛል። ብዙዎቹ የትውልዱ ልጆች በልዩ ሁኔታ ብሩህ ናቸው። የመገንዘብ አቅማቸው ከቀዳሚ ትውልዶች በጉልህ ሁኔታ የተለየ ሆኖ ይታያል።

 


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.