የኑሮ ውድነትን በማረጋጋት፣ የታለመላቸውን ግ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

የኑሮ ውድነትን በማረጋጋት፣ የታለመላቸውን ግብ እያሳኩ ያሉ የገበያ ማዕከላት በአዲስ አበባ!

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአምስቱ የከተማዋ መግቢያ-መውጫ በሮች፣ የመሰረታዊ ሸቀጦችን ዋጋ  ለማረጋጋት የሚረዱ፣ ከሶስተኛ ወገን ሰንሰለት ነፃ የሆነ ግብይት የሚከናወንባቸው ገበያ ማዕከላት ተገንብተዉ አገልግሎት እየሰጡ ሚገኙ ሲሆን ማዕከላቱ በላፍቶ ሁለ ገብ የገበያ ማእከል፣ አቃቂ ቃሊቲ፣ ለሚ ኩራ እና ኮልፌ ክፍለ ከተሞች የተገነቡ እና ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ፋይዳ ያላቸው ናቸው፡፡

ከዚህ ጎን-ለጎን ለህብረተሰቡ አማካይ እና አቅራቢያ በሆኑ ስፍራዎች የቅዳሜና እሁድ ገበያዎችን በጥራትና በስፋት በማቅረብ፣ በከተማዋ የሚታይ የኑሮ ውድነት ጫና ለማስቀረትና፣ ገበያውን ለማረጋጋት ከወሰዳቸው ዘርፈ ብዙ እርምጃዎች መካከል ግንባር ቀደም እና ለነዋሪው ትልቅ እፎይታን የሰጠ እና  የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጠ ተግባር ነው፡፡ 

በእነዚህ የገበያ ማዕከላት በሌማት ትሩፋትና በከተማ ግብርና ምርታማነትን በማሳደግ፣ ህብረተሰቡ ከሸማችነት ወደ አምራችነት እንዲሸጋገር ምቹ ሁኔታዎችን በመፍጠር እና ህገወጥ ንግድና ደላላን በማስቀረት፤ የመሰረታዊ ሸቀጦችን የዋጋ ንረት ለማረጋጋት የሚረዱ የግብርና ምርቶች በገበያ ማዕከላቱ በስፋት ተሰራጭተዉ ለሸማቹ ማህበረሰብ ተደራሽ እንዲሆኑ ሚናቸዉን በተጨባጭ እንዲወጡ አስችሏል፡፡


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.