አዲስ አበባ÷የሁላችን የጋራ አምባ፤ የአፍሪካ የ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

አዲስ አበባ÷የሁላችን የጋራ አምባ፤ የአፍሪካ የብልፅግና መልክ!

ውብ፣ ፅዱ እና ለነዋሪዎቿ ምቹ እና የአፍሪካ መዲና የሆነችዉ አዲስ አበባ፣ ታሪኳንና ባህሏን ከዘመናዊነት እና ቴክኖሎጂ ጋር አዋህዳ ሁለንተናዊ የብልፅግና ጉዞዋን በተግባር እያረጋገጠች ነው፡፡

ዓለም በአንድ ቃል! ምስክርነት ከሰጠባቸው የኮሪደር እና የወንዝ ዳር መሠረተ-ልማቶች በተጨማሪ ታሪኳንና ቅርሷን በማደስ በትላንት፣በዛሬና ነገ ፅኑ ድልድይ የገነባቻቸዉ ተጠቃሽ እና ትዕምርት የሆኑ በርካታ ሰዉ ተኮር ልማት ስራዎቿ ይገኙበታል፡፡

ዘርፈ-ብዙነትን ከተላበሱ የልማት ስራዎቿ፤-ልምድ መቀመርያ የሆኑ እና የነገ- ሀገር ተረካቢ የሆኑ ህፃናት ከቅድመ ወሊድ እስከ ትምህርት ቤት ምገባ ልዩ ትኩረት የምትሰጥበት የቀዳማይ ልጅነት ፕሮግራም፣ የቱሪስት የስህበት ማዕከል የሆኑ ፓርኮቿ፣ ህዝብ የጋራ ትውስታ እና ተዝናኖት የሚያሳልፍባቸው በርካታ ፕላዛዎች እና የህፃናት መጫወቻ ስፍራዎች፣ ደረጃቸውን የጠበቁ የእግረኛ እና ብስክሌት መንገዶች፣ የመሮጫ ትራኮች እና የተለያየ መጠን ያላቸው የስፓርት ሜዳዎች፣ ዘመናዊ የመኪና ፓርኪንግ እና ተርሚናሎች፣ግሪን የትራንስፖርት አማራጮች፣ ጥራት እና ስፋት ያለው የመንገድ መሰረተ-ልማቶች ጨምሮ በርካታ ዓለም አቀፍ እና አህጉር አቀፍ ኮንፈረንሶችን በብቃት የማስተናገድ ዓቅም የገነባች ከተማ፣ አዲስ አበባ ለመሆን በቅታለች፡፡

በሌላ በኩልም አገልግሎት አሰጣጥን የተሳለጠ እና ፍትሀዊ እንዲሆን የመሶብ አንድ ማዕከልን ከከተማ እስከ ክፍለ-ከተማ በመተግበር፤የተቋማትን አገልግሎት በቴክኖሎጂ በማስተሳሰር ቀላል፣ ምቹና ወጪ ቆጣቢ አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ እየሰራች ያለች ከተማ "አዲስ አበባ "የሁላችን የጋራ አምባ፤ የአፍሪካ የብልፅግና መልክ በመሆን ብዙ… ድንቅ ስራዎችን በተግባር አያጎናፀፈች ቀጥላለች፡፡


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.